መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“የሰው ልጆች ለሌሎች በጎ ነገር የማድረግ ችሎታ አላቸው። ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ በቃላት ለመግለጽ የሚያዳግቱ የክፋት ድርጊቶችን ሲፈጽሙ ይታያሉ። ሰዎች እንዲህ የሚያደርጉት ለምን እንደሆነ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ ይዟል። በተጨማሪም በጎ ምግባር ክፋትን እንዴት ድል እንደሚያደርግ ያብራራል።” ሮሜ 16:20ን አንብብ።
ንቁ! ጥር 2006
“ዓለማችን ከዛሬ 20 ወይም 30 ዓመታት በኋላ ምን ልትመስል እንደምትችል አስበው ያውቃሉ። [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም መዝሙር 119:105ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱ ጊዜ ምን ይዞ እንደሚመጣ ማስተዋል እንድንችል የእውቀት ብርሃን ያበራልናል። ይህ መጽሔት በጊዜ ሂደት ውስጥ የት ቦታ ላይ እንደምንገኝ የሚጠቁሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ይመረምራል። እንዲሁም ወደፊት የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለን መጠበቅ የምንችለው ለምን እንደሆነ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ጥር 15
“ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰዎች ለመላእክት የሚሰጡት ትኩረት እየጨመረ መጥቷል። ስለ መላእክት ማንነትና ሕይወታችንን እንዴት እንደሚነኩ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም መዝሙር 34:7ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ መላእክት ባለፉት ጊዜያት ምን እንዳከናወኑ፣ በአሁኑ ጊዜ ምን እየሠሩ እንዳሉ እንዲሁም ወደፊት ምን እንደሚሠሩ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ያብራራል።”
ንቁ! የካቲት 2006
“አብዛኞቻችን በዕድሜ የገፉ ዘመዶች አሊያም ጓደኞች አሉን። ሁላችንም ብንሆን እነዚህ ወዳጆቻችን ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ችግር እንዲቋቋሙ መርዳት የምንችልበትን መንገድ ብናውቅ ደስ ይለናል። አይደለም እንዴ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት አረጋውያን የዕድሜ መግፋትን ተከትለው የሚመጡትን ችግሮች እንዲቋቋሙ ለመርዳት ምን ማድረግ እንደሚቻል ሐሳብ ያቀርባል። በተጨማሪም አሁን የማነብልዎት ትንቢት እንዴት ፍጻሜውን እንደሚያገኝም ያብራራል።” ኢዮብ 33:25ን አንብብ።