መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“አብዛኞቹ ሃይማኖቶች ሰዎች ጎረቤቶቻቸውን ሊወድዱ እንደሚገባ ያስተምራሉ። [ማቴዎስ 22:39ን አንብብ።] ይህ ከሆነ ታዲያ በዓለም ላይ የሚካሄዱት አብዛኞቹ ጦርነቶችና ግጭቶች የሃይማኖት እጅ ያለባቸው ለምን ይመስልዎታል? [የሚሰጠውን መልስ አዳምጥ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ‘ሃይማኖት ለሰው ዘር አንድነት ሊያስገኝ ይችላል?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይዟል።”
ንቁ! ጥር 2005
“በዛሬው ጊዜ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እድገት ቢኖርም ይህ ሁኔታ የሰው ልጆች ጓደኛ ለማግኘት ያላቸውን መሠረታዊ ፍላጎት አላስቀረውም። ሆኖም በማኅብረሰቡ ውስጥ የሚታዩት ለውጦች የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረት አስቸጋሪ እንዲሆን ማድረጋቸውን ልብ ብለዋል? [የሚሰጠውን መልስ ካዳመጥህ በኋላ ምሳሌ 18:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት እውነተኛ ወዳጆች ማፍራትና ወዳጅነታችን ዘላቂ እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ ጥር 15
“ሁላችንም ለራሳችንም ሆነ ለልጆቻችን የተሻለ ሕይወት እንመኛለን። ሆኖም ብዙዎች ይህንን ለማግኘት አቅም እንደሌላቸው ይሰማቸዋል። የወደፊት ዕጣችንን መወሰን የምንችል ይመስልዎታል? [የሚሰጠውን መልስ አዳምጥ።] ይህ መጽሔት ሕይወታችንን መቆጣጠር እንደምንችልና የወደፊት ሕይወታችን አሁን በምናደርጋቸው ምርጫዎች ላይ የተመካ እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሰ ያብራራል።” ዘዳግም 30:19ን አንብብ።