መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“በዛሬው ጊዜ ብዙዎች ሥራ ማጣት ያሳስባቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ በሥራ ቦታ ያለባቸው ጫና ውጥረት ይፈጥርባቸዋል። አስደሳችና አስተማማኝ ሥራ ማግኘት የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ኢሳይያስ 65:21-23ን አንብብለት።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ሁሉም ሰው አስደሳች ሥራ የሚያገኝበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል።”
ንቁ! የካቲት 2003
“ዛሬ የምንኖረው ከምንጊዜውም ይበልጥ በደህንነታችን ላይ ስጋት ባጠላበት ዘመን ውስጥ ነው። ብዙዎች ገመናቸው ሳይቀር በሰዎች እየተደፈረ እንዳለ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ በደህንነታችን ላይ ስጋት የሚፈጥሩ ነገሮች ሙሉ በሙሉ እንደሚወገዱ ተስፋ ይሰጣል። [ኢሳይያስ 11:9ን አንብብ።] ይህ ተስፋ እንዴት እውን እንደሚሆን ይህ መጽሔት ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 15
“አንዳንድ ሰዎች አምላክ በእውን መኖሩን ይጠራጠራሉ። ሌሎች ደግሞ በአምላክ መኖር ቢያምኑም ሊቀርቡት እንደማይችሉ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አምላክን በቅርብ ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያሳያል። [ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] በዚህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ላይ ያሉት እነዚህ ሁለት ርዕሶች ይህንን በሚመለከት ግሩም ሐሳቦች ይዘዋል።”
Feb. 22
“አምላክ ትናንሽ ልጆችን ጨምሮ የሰው ዘር በአጠቃላይ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዲሠቃይ የሚፈልግ ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ይህንን የሚያጽናና ተስፋ ይመልከቱ። [መዝሙር 65:9ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት መንስኤ የሚሆኑትን ነገሮችና አምላክ በቅርቡ ይህንን ችግር እንደሚያስወግደው ይገልጻል።”