መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“ዛሬ ብዙ ሰዎች የጭቆናና የግፍ ሰለባ መሆናቸው የሚያስጨንቅ ነገር አይደለም? [በቅርቡ በአካባቢው የተከሰተን አንድ ነገር ጥቀስና መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት አምላክ ለሰው ልጅ ሕይወት ያለውን አመለካከት ያብራራል። በተጨማሪም በዛሬ ጊዜ ካሉት ሰቆቃዎች እንዴት እንደሚገላግለን ይገልጻል።” መዝሙር 72:12-14ን አንብብ።
ንቁ! የካቲት 2005
“አብዛኛው ሰው ለውበት ከልክ በላይ ትኩረት እንደሚሰጥ አስተውለዋል? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ለውጫዊ ውበት መጨነቅ የሚያስከትላቸውን አንዳንድ አደጋዎች ይገልጻል። በተጨማሪም የላቀ ግምት የሚሰጠው የውበት ዓይነት የቱ እንደሆነ ያብራራል።” 1 ጴጥሮስ 3:3, 4ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 15
“አንዳንድ ጊዜ የሆነ ተአምር እንደተፈጸመ የሚገልጹ ዘገባዎች እንሰማለን። [አንድ ምሳሌ ጥቀስ።] አንዳንድ ሰዎች እነዚህን ዘገባዎች ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ይጠራጠራሉ። ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙት ተአምራት በትክክል የተፈጸሙ ስለመሆናቸውና ዛሬም ተአምራት ይፈጸሙ እንደሆነና እንዳልሆነ ያስረዳል።” ኤርምያስ 32:21ን አንብብ።