መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“አብዛኞቻችን አካላዊ ጤንነታችንን ለመጠበቅ ጥረት እናደርጋለን። ይሁን እንጂ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንዳመለከቱት መንፈሳዊነታችንም በጤንነታችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህ አባባል ትክክል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ማቴዎስ 5:3ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም መንፈሳዊ ፍላጎታችንን እንዴት ማማሏት እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ! የካቲት 2004
“መድኃኒት የሚቋቋሙ ጀርሞች እየተበራከቱ የመምጣታቸው ጉዳይ የመነጋገሪያ ርዕስ እንደሆነ ልብ ብለዋል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ለእነዚህ ጀርሞች መበራከት መንስኤው ምን እንደሆነ የሚያብራራ ከመሆኑም በላይ ራሳችንን ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንደምንችል ሐሳብ ያቀርባል። ከዚህ በተጨማሪም ማንም የማይታመምበት ዓለም እንደሚመጣ የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይገልጻል።” ኢሳይያስ 33:24ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 15
“ብዙ ሰዎች በሃይማኖት ስም የሚካሄዱት መጥፎ ድርጊቶች ይረብሿዋል። አንዳንዶች የሰው ልጆች ችግሮች ዋነኛ መንስኤ ሃይማኖት እንደሆነ ይሰማቸዋል። ስለዚህ ጉዳይ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ራእይ 18:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ሐሳብ ያብራራል።”
Feb. 22
“ብዙ ሰዎች ስለ እንስሳት ማወቅ ያስደስታቸዋል፤ አንዳንዶች ደግሞ የቤት እንስሳት እንዲኖሯቸው ይፈልጋሉ። [ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት የቤት እንስሳትን መንከባከብ የሚያመጣቸውን አንዳንድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይገልጻል። ከዚህም በላይ ሁሉም እንስሳት እርስ በርሳቸውም ሆነ ከሰዎች ጋር በሰላም የሚኖሩበት ጊዜ እንደሚመጣ አምላክ ስለሰጠው ተስፋ ይናገራል።” ኢሳይያስ 11:6-9ን አንብብ።