መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“የሰው ልጆች መልስ ሊያገኙላቸው ያልቻሉ አንዳንድ ጥያቄዎች አሉ። ለምሳሌ፣ በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ጥያቄ ይመልከቱ። [ኢዮብ 21:7ን አንብብ።] እርስዎስ አምላክን መጠየቅ የሚፈልጉት ጥያቄ ይኖርዎት ይሆን? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በምድር ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ለሚያነሷቸው ሦስት አንገብጋቢ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ይሰጣል።”
ንቁ! ግንቦት 2003
“ዛሬ ብዙ ሰዎች በቂ እንቅልፍ እንደማያገኙ አስተውለዋል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ለዚህ ችግር ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያደርገው ውጥረት ወይም ጭንቀት ሊሆን ይችላል። [መክብብ 5:12ን አንብብ] ይህ መጽሔት እንቅልፍ እንድናጣ የሚያደርጉንን አንዳንድ ምክንያቶች የሚገልጽ ከመሆኑም በላይ የእንቅልፍ ልማዳችንን እንዴት ማሻሻል እንደምንችል ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦችን ይሰጣል።
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 15
“ስለ ዓመፅ ድርጊቶች የሚገልጹ ዜናዎችን በየዕለቱ እንሰማለን። ከአሁን ቀደም ዓመፅ የዚህን ያህል የተስፋፋበት ጊዜ የነበረ ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [ማቴዎስ 24:37ን አንብብ።] በኖህ ዘመን ዓመፅ በጣም ተስፋፍቶ ስለነበር አምላክ ከኖህና ከቤተሰቡ በስተቀር በወቅቱ የነበሩትን ሰዎች በሙሉ አጥፍቷቸዋል። ይህ መጽሔት በዚያን ጊዜ ከተፈጸሙት ሁኔታዎች ምን ትምህርት ማግኘት እንደምንችል ይገልጻል።”
May 22
“ነፍሳት አደገኛ የሆኑ በሽታዎችን ያስተላልፋሉ። ራሳችንን ለመከላከል ምን ማድረግ እንደምንችል ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ራሳችንን እንዴት መከላከል እንደምንችል የሚናገር ከመሆኑም በላይ መጽሐፍ ቅዱስ ማንኛውም ዓይነት በሽታ ስለሚወገድበት ጊዜ የሚሰጠውን ተስፋ ያብራራል።” ኢሳይያስ 33:24ን በማንበብ ደምድም።