መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“ሁሉም ሰው በሮሜ 12:17, 18 ላይ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ ቢያደርግ በዓለም ላይ የተሻለ ሁኔታ የሚኖር ይመስልዎታል? [ጥቅሱን ካነበብክለት በኋላ መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] አንዳንድ ጊዜ በግለሰቦች መካከል አለመግባባቶች የሚፈጠሩ መሆኑ ያሳዝናል። ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ አለመግባባቶችን ለማስወገድና ሰላም ለማስፈን እንዴት እንደሚረዳን ያሳያል።”
ንቁ! መጋቢት 2005
“ሁላችንም የጤና እክል ሲያጋጥመን ስሜታችንን የሚረዳልን ሐኪም ማግኘት ያስደስተናል። ይሁን እንጂ ስለ ሐኪማቸው ስሜት የሚያስቡት ምን ያህል ሕመምተኞች ናቸው? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ሐኪሞች የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች የሚገልጽ ከመሆኑም በላይ የሕክምናው መስክ የወደፊት ዕጣ ምን እንደሚሆን ያወሳል።” ኢሳይያስ 33:24ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 15
“በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሰዎች የኢየሱስን ትምህርቶች ያደንቃሉ። [በገጽ 3 አንቀጽ 1 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ አንብብ።] ሆኖም በማቴዎስ 5:21, 22ሀ ላይ የሚገኘውን ይህንን ነጥብ ጨምሮ ኢየሱስ ያስተማራቸው ነገሮች ዛሬ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ይመስልዎታል? [ጥቅሱን ካነበብክለት በኋላ መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ኢየሱስ ያስተማራቸውን ነገሮችና ከእነዚህም እንዴት ልንጠቀም እንደምንችል ያብራራል።”