መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“ይህ ስዕል የሚያሳየው የጌታ እራት ተብሎ የሚጠራው በዓል ሲከበር ነው። [የመጽሔቱን የፊትና የጀርባ ሽፋን አሳየው።] ክርስቲያኖች እንዲያከብሩት የታዘዙት ይህን በዓል ብቻ መሆኑን ያውቃሉ? [የሚሰጠውን መልስ አዳምጥ። ከዚያም ሉቃስ 22:19ን አንብብ።] ይህ በዓል መከበሩ በጣም አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያትና ለእርስዎም ምን ትርጉም እንዳለው ይህ መጽሔት ያብራራል።”
ንቁ! ሚያዝያ 2003
“አምላክ ትናንሽ ልጆችን ጨምሮ የሰው ዘር በአጠቃላይ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዲሠቃይ የሚፈልግ ይመስልዎታል? [የሚሰጠውን መልስ አዳምጥ።] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ይህንን የሚያጽናና ተስፋ ይመልከቱ። [መዝሙር 65:9ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት መንስኤ የሚሆኑትን ነገሮችና አምላክ በቅርቡ ይህንን ችግር እንደሚያስወግደው ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 15
“ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰዎች ለመንፈሳዊ እሴቶች የሚሰጡት ግምት እያሽቆለቆለ መምጣቱን አስተውለዋል? [የሚሰጠውን መልስ አዳምጥ። ከዚያም መዝሙር 119:105ን አንብብ።] መንፈሳዊ እሴቶች በሕይወታችን ውስጥ መጥፎ አካሄድ እንዳንከተል ያስችሉናል። ይህ መጽሔት ትክክለኛ መንፈሳዊ እሴቶችን ማግኘት የሚቻለው ከየት እንደሆነ ይጠቁማል።”
Apr. 22
“ብዙዎች በጊዜያችን ባለው ለውጥ በበዛበት ዓለም ውስጥ ልጆች ያለ ጊዜያቸው እያደጉ መሆናቸው ያሳስባቸዋል። ይህ እርስዎንስ አሳስቦዎት አያውቅም? [መልሱን አዳምጥ። ከዚያም መክብብ 3:1, 4ን አንብብ።] ልጆች ገና በልጅነታቸው የአዋቂዎችን ሸክም መሸከም የለባቸውም። ይህ የንቁ! እትም ወላጆች ልጆቻቸው የልጅነት ዕድሜያቸውን በሚገባ እንዲጠቀሙበት ማድረግ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”