ከደም እንድንርቅ ለመርዳት የተደረገ ዝግጅት
ቀን ያልታተመበት ወይም 3/99 የሚል ቀን የታተመበት የሕክምና አሰጣጥን የሚመለከት ማሳሰቢያ እና ባለሞያዎችን ከተጠያቂነት ነፃ የሚያደርግ ሰነድ ወይም መታወቂያ ካርድ ያላቸው የተጠመቁ አስፋፊዎች በዚህ ዓመት አዲስ ካርድ መሙላት አያስፈልጋቸውም። ታኅሣሥ 29 በሚጀምር ሳምንት በሚኖረው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የጉባኤው ጸሐፊ አዲስ ለተጠመቁ አስፋፊዎች፣ ለልጆቻቸው እና ካርዳቸውን መቀየር ለሚፈልጉ አስፋፊዎች በቂ ካርዶች ይዞ መምጣት አለበት። እነዚህ ቅጾች በየዓመቱ ለጉባኤዎች ከሚላኩት ቅጾች ጋር አብረው አይላኩም። ጉባኤው በቂ ካርዶች ከሌሉት ጸሐፊው በቅርብ ካሉ ጉባኤዎች ለማግኘት መጠየቅ ወይም ጉባኤው በሚልከው የጽሑፍ ማዘዣ ላይ ትእዛዝ መላክ ይችላል።
ካርዶቹን ቤት ወስዶ በጥንቃቄ መሙላት ይገባል፤ ሆኖም አይፈረምባቸውም። የካርዱ ባለቤትም ሆነ ምሥክሮች ካርዱ ላይ የሚፈርሙት እንዲሁም ቀን የሚጽፉበት በቀጣዩ የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ስብሰባ ላይ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቹ እርዳታ መጠየቅ ይቻላል። ምሥክር ሆነው የሚፈርሙ ወንድሞች/እህቶች የካርዱ ባለቤት ካርዱ ላይ ፊርማውን ሲያሰፍር ማየት አለባቸው።
አስፋፊዎች እጃቸው ላይ ባለው ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም በሚለው ሰነድ ላይ ያሰፈሩትን ሐሳብ መለወጥ ካልፈለጉ በስተቀር አዲስ ሰነድ መሙላት አያስፈልጋቸውም። ጸሐፊው ይህ ሰነድም ሆነ የሕክምና ሰነዶች አጠቃቀም መመሪያ የተባለው ሰነድ በበቂ መጠን ሊኖረው ይገባል።
ያልተጠመቁ አስፋፊዎች፣ የሕክምና አሰጣጥን የሚመለከት ማሳሰቢያ እና ባለሞያዎችን ከተጠያቂነት ነፃ የሚያደርግ ሰነድ፣ መታወቂያ ካርድ እንዲሁም ስለ ሕክምና ያለኝ የግል አቋም የተባሉትን ሰነዶች መሠረት በማድረግ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው የሕክምና መመሪያ በጽሑፍ ማዘጋጀት ይችላሉ።