የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች
በዚህ ዓመት የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው እሁድ፣ ሚያዝያ 4 ይሆናል። ሽማግሌዎች ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት መስጠት ይገባቸዋል:-
◼ ስብሰባው የሚደረግበትን ሰዓት ስትወስኑ ቂጣውና ወይኑ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር እንደሌለባቸው አስታውሱ።
◼ ተናጋሪውን ጨምሮ ሁሉም ተሰብሳቢዎች በዓሉ የሚከበርበት ትክክለኛ ጊዜና ቦታ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ ተገቢው ዓይነት ቂጣና ወይን ተዘጋጅቶ መቀመጥ አለበት።—የየካቲት 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14-15ን ተመልከቱ።
◼ ሳህኖች፣ ብርጭቆዎች እንዲሁም ተስማሚ የሆነ ጠረጴዛና የጠረጴዛ ልብስ ቀደም ብለው ወደ ስብሰባው አዳራሽ መጥተው በየቦታቸው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።
◼ የመንግሥት አዳራሹም ሆነ ሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ ቀደም ብሎ በሚገባ መጽዳት አለበት።
◼ አስተናጋጆች እንዲሁም ቂጣውንና ወይኑን የሚያዞሩ ወንድሞች ቀደም ብሎ ተመርጠው የሥራ ድርሻቸው፣ ሥራቸውን እንዴት በሚገባ ማከናወን እንደሚችሉና ሥርዓታማ የሆነ አለባበስና አበጣጠር አስፈላጊ መሆኑ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ አቅመ ደካማ በመሆናቸው በበዓሉ ላይ መገኘት የማይችሉ ቅቡዓን ከቂጣውና ከወይኑ መካፈል የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸት ይኖርበታል።
◼ በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች የሚጠቀሙ ከሆነ መግቢያው ላይ፣ የመኪና መንገድ ላይና በመኪና ማቆሚያው አካባቢ አላስፈላጊ ጭንቅንቅ እንዳይፈጠር በጉባኤዎቹ መካከል ጥሩ ቅንጅት ሊኖር ይገባል።