የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች
በዚህ ዓመት የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ረቡዕ ሚያዝያ 12 ይሆናል። ሽማግሌዎች የሚከተሉትን ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው ሊያስቡባቸው ይገባል።
◼ በዓሉ የሚጀምርበትን ሰዓት ስትወስኑ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ቂጣውና ወይኑ መዞር እንደሌለባቸው አስታውሱ።
◼ ተናጋሪውን ጨምሮ ሁሉም ሰው በዓሉ የሚከበርበትን ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ እንዲያውቅ መደረግ አለበት።
◼ ተገቢው ዓይነት ቂጣና ወይን ተዘጋጅቶ መቀመጥ አለበት።—የየካቲት 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14-15ን ተመልከቱ።
◼ ሳህኖች፣ ብርጭቆዎች፣ ለበዓሉ ተስማሚ የሚሆን ጠረጴዛና የጠረጴዛ ልብስ ቀደም ብሎ ወደ አዳራሹ ማምጣትና በቦታው ማስቀመጥ ያስፈልጋል።
◼ የመንግሥት አዳራሹ ወይም ለበዓሉ የምትጠቀሙበት ሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ አስቀድሞ በደንብ ሊጸዳ ይገባል።
◼ አስተናጋጆችም ሆኑ ቂጣና ወይኑን የሚያዞሩት ወንድሞች በቅድሚያ ሊመረጡና የሥራ ድርሻቸው ምን እንደሆነ፣ ሥራቸውን በተገቢው መንገድ እንዴት እንደሚያከናውኑ እንዲሁም ሥርዓታማ የሆነ አለባበስና አበጣጠር አስፈላጊ መሆኑ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ አቅመ ደካማ በመሆናቸው በበዓሉ ላይ መገኘት የማይችሉ ቅቡዓን ከቂጣውና ከወይኑ መካፈል የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸት ይኖርበታል።
◼ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች በመንግሥት አዳራሹ የሚጠቀሙ ከሆነ በመግቢያዎች አካባቢ፣ በመንገዱ ላይ እንዲሁም በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች አላስፈላጊ ጭንቅንቅ እንዳይፈጠር በጉባኤዎቹ መካከል ጥሩ ቅንጅት ሊኖር ይገባል።