የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/04 ገጽ 3
  • የወረዳ ስብሰባ ክለሳ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የወረዳ ስብሰባ ክለሳ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የልዩ ስብሰባ ቀን ክለሳ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • የወረዳና የልዩ ስብሰባዎችን ለመከለስ የተደረገ አዲስ ዝግጅት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • የወረዳ ስብሰባ ክለሳ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 9/04 ገጽ 3

የወረዳ ስብሰባ ክለሳ

ይህ ክፍል በ2005 የአገልግሎት ዓመት በሚካሄደው የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም ላይ የሚቀርበውን ትምህርት ለመከለስ የተዘጋጀ ሲሆን ስብሰባው ከመካሄዱ በፊትና ከተካሄደ በኋላ በጉባኤ ይቀርባል። በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 ላይ የቀረበው “የወረዳና የልዩ ስብሰባዎችን ለመከለስ የተደረገ አዲስ ዝግጅት” የሚለው ርዕስ ክለሳው ስለሚካሄድበት መንገድ ይናገራል። በክለሳው ወቅት ሁሉንም ጥያቄዎች ለመጠየቅ እንድትችል ጊዜህን በአግባቡ ከፋፍለህ ተጠቀምበት። ክለሳው በስብሰባው ላይ የቀረበውን ትምህርት እንዴት በሥራ ላይ ማዋል እንደምንችል የሚያጎላ መሆን አለበት።

የመጀመሪያው ቀን የጠዋት ፕሮግራም

1. አምላካዊ ጥበብ እንድናገኝ ምን ሊረዳን ይችላል?

2. ወረዳው ምሥራቹን በተቻለ መጠን ለብዙ ሰዎች ለማካፈል ምን ጥረት አድርጓል?

የመጀመሪያው ቀን የከሰዓት በኋላ ፕሮግራም

3. ክርስቲያኖች ውስጣዊ ንጽሕናቸውን መጠበቃቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንን የምናደርገውስ እንዴት ነው?

4. ከወንድሞቻችን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

5. ምክንያታዊ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው? በጊዜ አጠቃቀማችን ረገድ ምክንያታዊ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

6. ከሳኦልና ከኖኅ ምሳሌ ምን እንማራለን? “እሺ ባይ” መሆናችንን ማሳየት የምንችልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው? (ያዕ. 3:17)

7. ክርስቲያኖች ሁለት ዓይነት ኑሮ ላለመኖር መጠንቀቅ የሚችሉት እንዴት ነው?

8. የአምላክን ጥበብ በመናገር ረገድ የጳውሎስን ምሳሌ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው?

ሁለተኛው ቀን የጠዋት ፕሮግራም

9. ጊዜያችንን የምናሳልፍባቸውን እንቅስቃሴዎች ስንመርጥ ጠንቃቃ መሆን ያለብን ለምንድን ነው? በዚህ ረገድ ምን ሊረዳን ይችላል?

10. በወረዳው ያሉ አስፋፊዎች በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ አዘውትረው ለመገኘት ምን ጥረት እያደረጉ ነው? እንዲህ ማድረጋቸውስ ምን ጥቅም አስገኝቶላቸዋል?

11. የቤተሰብ ራሶች ቤተሰባቸውን በመንፈሳዊ መገንባት የሚችሉት እንዴት ነው?

12. ወረዳችንን በሚመለከት ምን ምን ነገሮችን ትኩረት ሰጥተን እንድናስተካከል ተበረታተናል?

ሁለተኛው ቀን የከሰዓት በኋላ ፕሮግራም

13. በሕዝብ ንግግሩ ላይ በተገለጸው መሠረት በአምላካዊ ጥበብ የተከናወኑ የጽድቅ ሥራዎችን ግለጽ።

14. በራሳችን ወይም በመለኮታዊ ጥበብ በማይመሩ ሰዎች መታመን ሞኝነት የሚሆነው ለምንድን ነው? በየትኞቹ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገናል?

15. መለኮታዊ ጥበብ ከየትኞቹ ወጥመዶች ይጠብቀናል?

16. በወረዳ ስብሰባው ፕሮግራም ላይ የቀረቡትን ምክሮች በሥራ ላይ ማዋላችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ