የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/05 ገጽ 11
  • የወረዳ ስብሰባ ክለሳ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የወረዳ ስብሰባ ክለሳ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የወረዳና የልዩ ስብሰባዎችን ለመከለስ የተደረገ አዲስ ዝግጅት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • የልዩ ስብሰባ ቀን ክለሳ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • የወረዳ ስብሰባ ክለሳ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 9/05 ገጽ 11

የወረዳ ስብሰባ ክለሳ

ይህ ክፍል በ2006 የአገልግሎት ዓመት በሚካሄደው የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም ላይ የሚቀርበውን ትምህርት ለመከለስ የተዘጋጀ ሲሆን ስብሰባው ከመካሄዱ በፊትና በኋላ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ይቀርባል። ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በመስከረም 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 ላይ በተገለጸው መሠረት ክፍሉ የሚቀርብበትን መንገድ ያመቻቻል። በክለሳው ወቅት ሁሉም ጥያቄ መቅረብ ያለበት በስብሰባው ላይ የተሰጠውን ትምህርት እንዴት በሥራ ላይ ማዋል እንደሚቻል በሚያጎላ መንገድ መሆን ይኖርበታል።

የመጀመሪያው ቀን

1. አዲሱን ሰው የምንለብሰው እንዴት ነው? አዲሱን ሰው እንደለበስን መቀጠል ያለብንስ ለምንድን ነው?

2. አንዳንዶች በስብከቱ ሥራ ላይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከፍ ያደረጉት እንዴት ነው?

3. ራሳችንን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የሌለብን ለምንድን ነው?

4. እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የአዲሱን ሰው ባሕርያት በቤተሰቡ ክልል ውስጥ እንዴት ማንጸባረቅ ይችላል?

5. ጉባኤውን በታማኝነት እንደምንደግፍ እንዴት ማሳየት እንችላለን?

6. በመስክ አገልግሎታችን የአዲሱን ሰው ባሕርያት ማሳየት የሚኖርብን ለምንድን ነው?

7. ተገቢ የሆነ ማሰላሰል ምን ነገሮችን ያካትታል? እንዲህ ዓይነቱ ማሰላሰል የሚጠቅመንስ በምን መንገድ ነው?

8. የይሖዋ እጅ በተፈለገው መንገድ እንዲቀርጸን የትኞቹ ባሕርያት ያስፈልጉናል?

ሁለተኛው ቀን

9. አንደበታችንን በአግባቡ መጠቀማችን ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

10. ከሥራ ባልደረቦቻችን፣ ከትምህርት ቤት ጓደኞቻችን እንዲሁም ከሌሎች ጋር የምናደርገው ጭውውት የሚያንጽ መሆኑ ምን ጥቅሞችን ያስገኝልናል?

11. ጳውሎስ በኤፌሶን 4:25-32 ላይ ከእምነት አጋሮቻችን ጋር ሊኖረን የሚገባውን ግንኙነት አስመልክቶ የሰጠውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

12. አንደበታችንን እጅግ ለከበረ አገልግሎት ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት ነው?

13. ክፉውን ለማሸነፍ ምን ማድረግ ይገባናል?

14. የዓለም ርኩሰት እንዳይጋባብን በየትኞቹ መስኮች ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል?

15. ውስጣዊ ሰውነታችንን በየዕለቱ ማደስ ያለብን ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?

16. በዚህ የወረዳ ስብሰባ ላይ ልትሠራበት የሚገባ ምን ትምህርት አግኝተሃል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ