የልዩ ስብሰባ ቀን ክለሳ
ይህ ክፍል በ2005 የአገልግሎት ዓመት በሚካሄደው የልዩ ስብሰባ ፕሮግራም ላይ የሚቀርበውን ትምህርት ለመከለስ የተዘጋጀ ሲሆን ስብሰባው ከመካሄዱ በፊትና ከተካሄደ በኋላ ይቀርባል። በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 ላይ የቀረበው “የወረዳና የልዩ ስብሰባዎችን ለመከለስ የተደረገ አዲስ ዝግጅት” የሚለው ርዕስ ክለሳው ስለሚካሄድበት መንገድ ይናገራል። በክለሳው ወቅት ሁሉንም ጥያቄዎች ለመጠየቅ እንድትችል ጊዜህን በአግባቡ ከፋፍለህ ተጠቀምበት። ክለሳው በስብሰባው ላይ የቀረበውን ትምህርት እንዴት በሥራ ላይ ማዋል እንደምንችል የሚያጎላ መሆን አለበት።
የጠዋት ፕሮግራም
1. ከምንጊዜውም በበለጠ በዘመናችን ይሖዋን ማዳመጥ የሚኖርብን ለምንድን ነው? ማዳመጥ ሲባል ምን ማለት ነው? (“የይሖዋን ድምፅ ማዳመጥ ያለብን ለምንድን ነው?”)
2. ቤተሰቦች ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ እንዲኖራቸው ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? (“ትኩረታቸው ሳይሰረቅ የአምላክን ቃል የሚያዳምጡ ቤተሰቦች”)
3. በወረዳው ውስጥ ያሉ አስፋፊዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመመሥከር ምን ተሞክሮዎች አግኝተዋል? (“የምታደርጉትን ሁሉ ለአምላክ ክብር አድርጉት”)
4. በዕብራውያን ምዕራፍ 3ና 4 ላይ ከሚገኘው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን? በጊዜያችን የይሖዋን ድምፅ የምንሰማው በማን በኩል ነው? (“አምላክ ሲናገር ማዳመጣችን ጥበቃ ያስገኝልናል”)
5. ከጥምቀት ንግግሩ ምን ጥቅም አግኝተሃል? (“ራስን መወሰንና ጥምቀት”)
የከሰዓት በኋላ ፕሮግራም
6. ኢየሱስ ወጣት ሳለ ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን? በወረዳው ውስጥ ያሉ ወጣቶችስ የእርሱን ምሳሌ እየኮረጁ ያሉት እንዴት ነው? (“ወጣቶች የአምላክን ቃል በትኩረት ማዳመጣቸው ጥንካሬ የሚሰጣቸው እንዴት ነው?”)
7. ወላጆች ልጆቻቸውን ከሕፃንነታቸው አንስቶ እንዲሁም ከፍ እያሉ ሲሄዱ በይሖዋ መንገዶች ሊያሠለጥኗቸው የሚችሉት እንዴት ነው? (“አምላክን በማዳመጥ ትምህርት የሚቀስሙ ሕፃናት”)
8. በተለይ በየትኞቹ ጉዳዮች ይሖዋን፣ ልጁንና ‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ ማዳመጥ ይኖርብናል? (ማቴዎስ 24:45 የ1954 ትርጉም ) እንዲህ ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (“አምላክ የሚሰጣችሁን ትምህርት ምንጊዜም በትኩረት አዳምጡ”)