ለቤተሰባችሁ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም አውጡ
1 ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ አድማጮቹን “ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ” በማለት አሳስቧቸዋል። (ማቴ. 6:33) ቤተሰባችሁ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ለመንፈሳዊ ነገሮች ቅድሚያ መስጠት እንድትችሉ ፕሮግራማችሁን በጽሑፍ ማስፈር ጠቃሚ ነው። ጥቂት ደቂቃዎች ወስዳችሁ በዚህ አባሪ ገጽ 6 ላይ የሚገኘውን ፕሮግራም በመጠቀም የራሳችሁን ሳምንታዊ የቤተሰብ ፕሮግራም ማውጣት ትችላላችሁ። አንዳንዶች ዕለታዊ እንቅስቃሴያቸውን ወረቀት ላይ ጽፈው እየቆረጡ ፕሮግራሙ ላይ መለጠፍ ይመርጣሉ፤ ሌሎች ደግሞ እዚያው ፕሮግራሙ ላይ መጻፍ ይፈልጉ ይሆናል።
2 ከዚህ በታች የቀረበው የናሙና ፕሮግራም የራሳችሁን ፕሮግራም ለማውጣት ሊረዳችሁ ይችላል። የናሙና ፕሮግራሙ የሚከተሉትን አራት መሠረታዊ ነገሮች ብቻ የያዘ መሆኑን ልብ በሉ:- (1) በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት፣ (2) በቤተሰብ ደረጃ አብሮ ማገልገል፣ (3) የቤተሰብ ጥናት እና (4) በዕለት ጥቅሱ ላይ የሚደረግ ውይይት። እነዚህን በፕሮግራማችሁ ውስጥ ማካተታችሁ “ከሁሉ የሚሻለውን ለይታችሁ እንድታውቁ” ይረዳችኋል። (ፊልጵ. 1:10) እነዚህን አራት መስኮች በተመለከተ በገጽ 4 እና 5 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦች ቀርበዋል።
3 የቤተሰብ ፕሮግራማችሁ በእነዚህ አራት መስኮች ብቻ የተወሰነ መሆን የለበትም። ለአንዳንድ ስብሰባዎች አንድ ላይ የምትዘጋጁ ከሆነ በፕሮግራሙ ላይ ልትጽፉት ይገባል። ከዕለት ጥቅስ በኋላ ወይም በሌላ ወቅት ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተወሰነ ምዕራፍ አንድ ላይ ሆናችሁ የምታነቡ ከሆነ ይህንንም ልታካትቱ ትችላላችሁ። ቤተሰቡ አንድ ላይ ሆኖ የመዝናናት ልማድ ካለው ይህም በፕሮግራሙ ውስጥ መካተት ይችላል።
4 የቤተሰብ ፕሮግራሙ ከቤተሰቡ አባላት ሁኔታና ፍላጎት ጋር የሚስማማ መሆን ይኖርበታል። የፕሮግራሙን ውጤታማነት በየጊዜው በመገምገም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማስተካከያዎች አድርግ።
[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሰንጠረዥ]
የቤተሰብ ፕሮግራም ናሙና
ጠዋት ከሰዓት በኋላ ማታ
እሁድ የዕለት ጥቅስ
የሕዝብ ስብሰባና
የመጠበቂያ ግንብ ጥናት
ሰኞ የዕለት ጥቅስ የቤተሰብ ጥናት
ማክሰኞ የዕለት ጥቅስ የጉባኤ
መጽሐፍ ጥናት
ረቡዕ የዕለት ጥቅስ
ሐሙስ የዕለት ጥቅስ ቲኦክራሲያዊ
የአገልግሎት ትምህርት ቤትና
የአገልግሎት
ስብሰባ
ዓርብ የዕለት ጥቅስ
ቅዳሜ የዕለት ጥቅስ
ከቤተሰብ ጋር
ማገልገል
(የመጽሔት ቀን)
[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሰንጠረዥ]
የቤተሰብ ፕሮግራም
ጠዋት ከሰዓት በኋላ ማታ
እሁድ
ሰኞ
ማክሰኞ
ረቡዕ
ሐሙስ
ዓርብ
ቅዳሜ
................................................................................
የዕለት ጥቅስ የዕለት ጥቅስ የዕለት ጥቅስ የዕለት ጥቅስ የዕለት ጥቅስ የዕለት ጥቅስ የዕለት ጥቅስ
ጥቅስ ጥቅስ ጥቅስ ጥቅስ ጥቅስ ጥቅስ ጥቅስ
የሕዝብ ቲኦ- የጉባኤ- የቤተሰብ ከቤተሰብ የቤተሰብ ከቤተሰብ
ስብሰባ ክራሲያዊ መጽሐፍ ጥናት ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ ጋር
እና የአገልግሎት ጥናት ማገልገል ንባብ መዝናናት
የመጠበቂያ- ትምህርት ቤት
ግንብ እና
ጥናት የአገልግሎት
ስብሰባ