መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“ሁላችንም ሕይወታችንን ለመምራት ገንዘብ ያስፈልገናል። ይሁንና እዚህ ጥቅስ ላይ ከተጠቀሰው አደጋ መጠንቀቅ ይኖርብናል ቢባል አይስማሙም? [1 ጢሞቴዎስ 6:10ን አንብብና መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ቁሳዊ ብልጽግና የሚያስከትላቸውን አንዳንድ አደገኛ ሁኔታዎች ከመጠቆሙም በላይ ምን ጥንቃቄ ማድረግ እንደምንችልም ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 15
“መላውን ዓለም የሚያስተዳድር አንድ ገዥ የመምረጥ አጋጣሚ ቢሰጥዎ ማንን ይመርጡ ነበር? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት አምላክ ምድርን እንዲገዛ የመረጠው መሲሕ ለዚህ ቦታ ብቁ እንደሆነ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ይዟል። እንዲሁም የመሲሑ አገዛዝ ለሰው ልጆች ምን እንደሚያመጣላቸው ያብራራል።” ኢሳይያስ 9:6, 7ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“ብዙ ሰዎች፣ ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ላይ ባዘዘን መሠረት እርስ በርሳችን መዋደድ እንዳለብን ይስማማሉ። [ዮሐንስ 13:34, 35ን አንብብ።] ይሁንና የኢየሱስን ትምህርቶች በሕይወታቸው ተግባራዊ የሚያደርጉት እነማን ናቸው? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት እውነተኛ ክርስቲያኖችን እንዴት ለይተን ማወቅ እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ! መጋቢት 2006
“ፍቅር ለደስታችንም ሆነ ለጤንነታችን በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ሆኖም ብዙ ሰዎች እውነተኛውን ፍቅር ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ይህ የሆነው ለምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] እውነተኛ ፍቅር ለማግኘት ከሚረዱን ቁልፍ ነገሮች አንዱ ለሌሎች ከራስ ወዳድነት ነጻ የሆነ ፍቅር ማሳየት ነው። ይህ መጽሔት እንዲህ ማድረጉ ምን ነገሮችን እንደሚያካትት ያብራራል።” 1 ቆሮንቶስ 13:4-7ን አንብብ።