በሕይወታችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል?
1 ልጆች አንዳንድ ጊዜ “ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?” ተብለው ይጠየቃሉ። ትንሽ ልጅ እያለህ ዶክተር፣ ፓይለት ወይም የወረዳ የበላይ ተመልካች ብለህ መልሰህ ነበር? ወይም ትንሽ ልጅ ሳለሽ ሆስተስ፣ ነርስ ወይም ቤቴላዊ ብለሽ መልሰሽ ነበር? አሁን ግን አድጋችሁ ትልልቆች ስለሆናችሁ ‘ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል?’ ብላችሁ ራሳችሁን መጠየቅ ይኖርባችኋል። ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ?
2 የይሖዋ ድርጅት ከሁሉ የተሻለ ውሳኔ ማድረግ እንድትችሉ ለመርዳት የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? የሚል ዲቪዲ አዘጋጅቶላችኋል። ድራማውን፣ ቃለ ምልልሱንና ተጨማሪ ክፍሉን ጨምሮ በፊልሙ ውስጥ የተካተቱትን ክፍሎች ሁሉ ትኩረት ሰጥታችሁ ተመልከቷቸው። በዲቪዲው ላይ የተካተቱት ነገሮች “ሜይን ሜኑ” (Main Menu) በሚለው ዋና ማውጫ ውስጥ ይገኛሉ።
3 ድራማው:- ድራማውን ስትመለከት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:- (1) በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ በተጠቀሰው በጢሞቴዎስና በአንድሬ መካከል ምን ተመሳሳይነት አለ? (ሥራ 16:1፤ 1 ጢሞ. 4:8፤ 2 ጢሞ. 1:5) (2) አንድሬ በአትሌቲክሱ ይበልጥ እንዲገፋበት ግፊት የሚደረግበት እንዴት ነበር? ግፊት የሚያደርጉበትስ እነማን ነበሩ? (3) ጢሞቴዎስና አንድሬ ትክክለኛ ምርጫ እንዲያደርጉ በጎ ተጽዕኖ ያሳደሩባቸው እነማን ናቸው? በምንስ መንገድ? (2 ጢሞ. 1:1-4፤ 3:14, 15) (4) በማቴዎስ 6:24 እና በፊልጵስዩስ 3:8 ላይ የሚገኙት ምክሮች አንድሬ በአስተሳሰቡ ላይ ለውጥ እንዲያደርግ የረዱት እንዴት ነው? እነዚህ ጥቅሶች አንተንስ የሚነኩት እንዴት ነው?
4 የተመረጡ ትዕይንቶች (Selected Scenes):- ሙሉውን ድራማ ካየህ በኋላ የሚከተሉትን ትዕይንቶች ደግመህ በመመልከት እነዚህን ጥያቄዎች መልስ። “ጳውሎስና ጢሞቴዎስ”:- ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የሰጠው የመጨረሻ ምክር ምን ነበር? (2 ጢሞ. 4:5) “ለይሖዋ ምርጥህን መስጠት”:- ምን መንፈሳዊ ግቦች አሉህ? “ከይሖዋ ጎን መቆም”:- እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ከየት ነው? “የአያቱ ምክር”:- በሰይጣን ዓለም ውስጥ ዝነኛ ወይም ኮከብ ለመሆን መፈለግ ምን ችግር አለው? (ማቴ. 4:9) “አልጸጸትም”:- በሕይወትህ ስኬታማ እንድትሆን የሚረዳህ ምን ነገር አገኘህ?—ምሳሌ 10:22
5 ቃለ ምልልሶች (Interviews):- ሴክሽንስ (sections) በሚለው ውስጥ ያሉትን የሚከተሉትን ክፍሎች ስትመለከት ለይሖዋ ምርጥህን ለመስጠት የሚያስችል ምን ነገር አስተዋልክ? (1) “ራስህን የወሰንከው ከንቱ ለሆኑ ነገሮች ነው ወይስ ለአምላክ?” (1 ዮሐ. 2:17)፤ (2) “ከአገልግሎትህ ደስታ ለማግኘት ጣር” (መዝ. 27:14)፤ (3) “ለአገልግሎት የተከፈተ በር።”—ማቴ. 6:33
6 ስላደረጉት ውሳኔ መለስ ብለው ሲያስቡ (Looking Back):- የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ትችላለህ? (1) ወንድምና እህት የመረጡት የሥራ መስክ ምን ዓይነት ነበር? ለምንስ? (2) ምን ያህል ተሳክቶላቸዋል? (3) እያንዳንዳቸው በሕይወታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲያደርጉ የረዳቸው ምን ነበር? (2 ቆሮ. 5:15) (4) ቀድሞ ይሮጡላቸው የነበሩትን ነገሮች ከተዉ በኋላ ምን ዓይነት ቲኦክራሲያዊ ግቦችን መከታተል ጀመሩ? ሁለቱንም ግቦች በአንድ ላይ ማስኬድ እንደማይችሉ የተሰማቸው ለምንድን ነው? (5) የሕይወት አቅጣጫቸውን በመቀየራቸው ተጸጽተዋል? (6) እነርሱ ከተናገሩት ውስጥ የሕይወትህን አቅጣጫ በተመለከተ ቆም ብለህ እንድታስብ ያደረገህ የትኛው ነው?
7 ተጨማሪ ቃለ ምልልሶች (Supplementary Interviews):- በእነዚህ ቃለ ምልልሶች ውስጥ ይሖዋን ይበልጥ ለማገልገል የሚረዳህ ምን ትምህርት አግኝተሃል? (1) “የግል ጥናት ያለው ጠቀሜታ፣” (2) “ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሉ አማራጭ መንገዶች፣” (3) “የቤቴል አገልግሎት፣” (4) “ጊልያድ የሚስዮናውያን ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት” እና (5) “የአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት።”—“ከእነዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጽሑፎች ማውጫ” (Index to Published Information on Related Subjects) የሚለውን ተመልከትና አንተን ይበልጥ የሚስብህን ርዕሰ ጉዳይ አንብብ።
8 ታዲያ ሕይወትህን እንዴት መጠቀም እንደሚኖርብህ ወሰንክ? ጳውሎስ ጢሞቴዎስን “ሰው ሁሉ ማደግህን ያይ ዘንድ በእነዚህ ነገሮች ላይ አትኲር፤ በትጋትም ፈጽማቸው” በማለት አሳስቦታል። (1 ጢሞ. 4:15) እኛም በዚህ ዲቪዲ ላይ ካያችሁትና ከሰማችሁት ጋር የሚስማማ ነገር እንድታደርጉ እናሳስባችኋለን። ይሖዋ በአሁኑ ጊዜ ደስተኛና ስኬታማ እንድትሆኑ ለወደፊቱም በረከት እንድታገኙ የሚያስችላችሁን ጥበብ የተሞላበት ውሳኔ ማድረግ እንድትችሉ እንዲረዳችሁ ጠይቁት።
[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
MAIN MENU
Play Drama
Scenes (11 selections)
Interviews
Play All
Sections (3 selections)
Looking Back
Supplementary Material
Supplementary Interviews
Index to Published Information on Related Subjects
Subtitles
Hearing Impaired
None
To navigate around the menus, use the Next ▶, ◀ Back, and Main Menu buttons.
ከላይ የተዘረዘሩትን በዲቪዲው ላይ የተካተቱ ክፍሎች ከፍተህ ለማየት Next ▶፣ ◀ Back እና MAIN MENU የሚሉትን ምርጫዎች ተጠቀም።