የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? (ክፍል 1)
ወጣቶች ወደ አዋቂነት ለመሸጋገር በሚያደርጉት ጉዞ ከባድ ውሳኔዎችን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? የተባለው ቪዲዮ የተዘጋጀው በዚህ ረገድ ወጣቶችን ለመርዳት ታስቦ ነው። በዋናው መምረጫ ላይ የሚገኘውን Play Drama (ድራማውን አጫውት) የሚለውን ምርጫ ከከፈታችሁ በኋላ በአንቀጽ 2 ውስጥ የሚገኙትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ። ከዚያም በዋናው መምረጫ ላይ Interviews (ቃለ ምልልሶች) የሚለውን ከመረጣችሁ በኋላ የምታገኙትን Looking Back (መለስ ብሎ ማሰብ) የሚለውን ክፍል ከተመለከታችሁ በኋላ በአንቀጽ 3 ውስጥ የሚገኙትን ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት አድርጉ።
ድራማ፦ (1) በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ክርስቲያን ወጣቶች ያሉበት ሁኔታ ጢሞቴዎስ ከነበረበት ሁኔታ ጋር የሚመሳሰለው በየትኞቹ መንገዶች ነው? (2) አንድሬ በአትሌቲክስ ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ጫና የተደረገበት እንዴት ነው? (3) ወንድም ፍላይሲግ ስለሚከተሉት ነገሮች ለአንድሬ ምን ሐሳብ አካፈለው? (ሀ) ለይሖዋና ለስፖርት ያደሩ ስለመሆን። (ማቴ. 6:24) (ለ) ስለ እውነተኛ ደስታ ምንጭ። (ሐ) በማጎሪያ ካምፕ ሳለ ይጠቀምበት የነበረው ሳህን ስለሚያስታውሰው ነገር። (መ) ከእሱና ከባለቤቱ ጋር በፎቶግራፉ ላይ ስለሚታዩት ሰዎች። (ሠ) ይመኘው የነበረውን ነገር በመተዉ ይቆጨው እንደሆነ ስለጠየቀው ጥያቄ። (ፊልጵ. 3:8) (4) አንድሬ “ኮኮብ ሯጭ መሆኔ ስህተት ነው?” በማለት ላቀረበው ጥያቄ አያቱ ምን ምላሽ ሰጠችው? (ሉቃስ 4:5-7) (5) አንድሬ ውድድሩን ማሸነፉ እውነተኛ እርካታ አስገኝቶለታል? (6) ወንድም ፍላይሲግ ለአንድሬ ከጻፈለት የስንብት ደብዳቤ ላይ ልብህን የነካው የትኛው ሐሳብ ነው? (ምሳሌ 10:22) (7) ወንድም ፍላይሲግ አንድሬን የረዳው ምን ነገር እንዲገነዘብ ነው?
መለስ ብሎ ማሰብ፦ (8) ወንድምና እህት ምን ዓይነት ሥራ ነበራቸው? ይህን ሙያ የመረጡትስ ለምንድን ነው? (9) በሙያቸው ምን ያህል ስኬታማ ነበሩ? (10) በሕይወታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲያደርጉ ያነሳሳቸው ነገር ምንድን ነው? (2 ቆሮ. 5:15) (11) የቀድሞ ሥራቸውን በየትኞቹ ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ተኩ? ሁለቱንም ጎን ለጎን ማስኬድ እንደማይችሉ የተሰማቸውስ ለምንድን ነው? (12) በሕይወታቸው ውስጥ ትልቅ ቦታ በሚሰጡት ነገር ላይ ለውጥ በማድረጋቸው ተጸጽተዋል? (13) ከተናገሩት ሐሳብ መካከል ሕይወትህን ስለምትጠቀምበት መንገድ ቆም ብለህ እንድታስብ ያደረገህ የትኛው ነው?
በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ በተቀሩት ቃለ ምልልሶችና በተጨማሪ ክፍሉ ላይ ውይይት ሲደረግ ሐሳብ ለመስጠት እንድትችሉ እባካችሁ እነዚህን ክፍሎች ተመልከቷቸው።