የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? (ክፍል 2)
የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? በተባለው ቪዲዮ ዋና መምረጫ ላይ Interviews (ቃለ ምልልሶች) የሚለውን ከመረጣችሁ በኋላ Sections (ክፍሎች) የሚለውን ክፍል ክፈቱ። በዚህ ሥር የሚገኙትን ሦስቱንም ክፍሎች ከተመለከታችሁ በኋላ አንቀጽ 2 ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎች በመጠቀም ሐሳቡን ከልሱ። ከዚያም በዋናው መምረጫ ላይ Supplementary Material (ተጨማሪ ክፍል) በሚለው ውስጥ የሚገኙትን አምስት ተጨማሪ ቃለ ምልልሶች በመመልከት በአንቀጽ 3 ውስጥ ለሚገኙት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሞክሩ።
ክፍሎች—ራስህን የወሰንከው ከንቱ ለሆኑ ነገሮች ነው ወይስ ለአምላክ? (1) ወጣቶች ምን ዓይነት ግቦችን እንዲያሳድዱ ተጽዕኖ ይደረግባቸዋል? (2) በ1 ዮሐንስ 2:17 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ወጣቶች እስከ ምን ድረስ ዓለማዊ ትምህርት መከታተል እንዳለባቸው ለመወሰን የሚረዳቸው እንዴት ነው? (3) ፍርሃት ከመጠመቅ እንዲያግደን መፍቀድ የሌለብን ለምንድን ነው? (4) ለጥምቀት ዝግጁ እንድንሆን ከሚረዱን ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? ከአገልግሎትህ ደስታ ለማግኘት ጣር፦ (5) አንዳንዶች ከአገልግሎት ደስታ የማያገኙት ለምንድን ነው? (6) ከአገልግሎታችን ደስታ ለማግኘት የሚረዱን አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው? (7) አንዳንዶች የማያውቁትን ሰው ከማነጋገር የበለጠ የሚያስፈራቸው ምንድን ነው? ለምንስ? (8) ፍርሃታችንን ማሸነፍና የመናገር ድፍረት ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው? (9) በአገልግሎት የተካንን መሆናችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ለአገልግሎት የተከፈተ በር፦ (10) አቅኚነት በመንፈሳዊ እድገት ለማድረግ የሚረዱ በርካታ አጋጣሚዎች የሚከፍትልን እንዴት ነው? (ፊልጵ. 3:16) (11) ብዙዎች በአቅኚነት ለመካፈል የሚያመነቱት ለምንድን ነው? (12) በገንዘብ ረገድ የሚያስጨንቁንን ነገሮች ለማሸነፍ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊረዱን ይችላሉ? (13) አንዳንዶች በአቅኚነት አገልግሎት እየተካፈሉ ራሳቸውን ለማስተዳደር ምን አድርገዋል? (14) አንድ ሰው ያለበት ሁኔታ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለመካፈል የማይፈቅድለት ከሆነ ምን ማድረግ ይችላል?
ተጨማሪ ክፍል—የግል ጥናት ያለው ጠቀሜታ፦ (15) ጥሩ የግል ጥናት ልማድ ማዳበር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? አማራጭ የስብከት ዘዴ (አሁን የአደባባይ ምሥክርነት ተብሏል)፦ (16) በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች መካፈላችን ደስታችንን የሚጨምርልን እንዴት ነው? የቤቴል አገልግሎት፦ (17) የቤቴል አገልግሎት ምን ዓይነት ደስታ ያስገኛል? የአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት፦ (18) በዚህ ትምህርት ቤት (አሁን ለነጠላ ወንድሞች የተዘጋጀ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ተብሏል) የተካፈሉ ወንድሞች ምን ጥቅም አግኝተዋል? ጊልያድ የሚስዮናውያን ማሠልጠኛ፦ (19) ፒተርና ፊዮና ለሚስዮናዊነት አገልግሎት ራሳቸውን ያዘጋጁት እንዴት ነው? ጊልያድ በመግባታቸው የተጠቀሙትስ እንዴት ነው?