መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“አንዳንድ ሰዎች የተለየ ዘር ወይም ዜግነት ስላላቸው አሊያም ሌላ ቋንቋ ስለሚናገሩ ብቻ በደል የሚደርስባቸው ለምን እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ምክንያቱ ምን እንደሆነ ይመልከቱ። [1 ዮሐንስ 4:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ‘ሁሉም ዘሮች ተስማምተው መኖር ይችሉ ይሆን?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።”
ንቁ! ሐምሌ 2007
“በደመ ነፍስ ከሚመሩት እንስሳት በተለየ መልኩ ሰዎች ሕይወታቸውን የሚመሩበትን መሥፈርት የመምረጥ ችሎታ አላቸው። ታዲያ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምንችለው ከየት ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም መዝሙር 119:105ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈሩት መመሪያዎች የላቁ እንደሆኑ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 15
“የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት ከፍተኛ ሐዘን ሊያስከትል ይችላል። እርስዎ፣ ሰዎች ከሞቱ በኋላ በውስጣቸው የምትገኝ አንዲት ነገር በሕይወት መኖሯን ትቀጥላለች ብለው ያምናሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ኢየሱስ እንዲህ በማለት አበረታች ተስፋ ሰጥቷል። [ዮሐንስ 5:28, 29ን አንብብ።] ኢየሱስ ትንሣኤ የሚከናወንበት ጊዜ ‘እንደሚመጣ’ ተናግሯል። ይህ መጽሔት፣ ሙታን በአሁኑ ወቅት ስላሉበት ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ማብራሪያ ይዟል።”
ንቁ! ነሐሴ 2007
“ወላጆች ጠቃሚ ምክር ማግኘት የሚችሉት ከየት ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረውን ይህን ሐሳብ ልብ ይበሉ። [2 ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ወላጆች ልጆቻቸውን ደስተኛ እንዲሆኑ አድርገው በማሳደግ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ ስላለው ጥቅም ይናገራል።”