የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/08 ገጽ 2
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘በተገቢው ጊዜ የቀረበ ምግብ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • የ2010 የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 11/08 ገጽ 2

አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም

የ2009 የአገልግሎት ዓመት የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም ‘አገልግሎቱን ከፍጻሜ እንድታደርሱ ለአገልግሎቱ ትኩረት መስጠታችሁን ቀጥሉ’ የሚል ጭብጥ ያለው ሲሆን በቆላስይስ 4:17 [NW] ላይ የተመሠረተ ነው። ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ይህን ምክር በቁም ነገር እንመለከተዋለን። ዓላማችን አገልግሎታችንን በታማኝነት መፈጸም ነው፤ ኢየሱስም እንኳ ያደረገው ይህንኑ ነው። (ዮሐ. 17:4) በዚህ ረገድ ሐዋርያው ጳውሎስም በጣም ግሩም ምሳሌ ትቶልናል። ጀምሮት የነበረውን አገልግሎት ወደ ፍጻሜው ለማድረስ ቆርጦ ነበር።—ሥራ 20:24

የወረዳ የበላይ ተመልካቹ የሚያቀርበው ንግግር የተለያዩ አስፋፊዎች በአገልግሎታቸው የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዴት እየተወጧቸው እንዳሉ ያሳያል። “የተከላችሁትን ኮትኩቱት” የሚለው ንግግር ‘ለዘላለም ሕይወት የተዘጋጁትን’ ሰዎች እንዴት መርዳት እንደምንችል ጎላ አድርጎ ይገልጻል። (ሥራ 13:48) ጎብኚ ተናጋሪው “ራሳችንን አገልጋዮች አድርገን የምናቀርበው እንዴት ነው?” በሚለው ንግግር አማካኝነት 2 ቆሮንቶስ 6:1-10ን ቁጥር በቁጥር ያብራራል። ከሰዓት በኋላ ደግሞ “ለአገልግሎታችሁ ከፍ ያለ ግምት ይኑራችሁ” በሚል ርዕስ ንግግር ያቀርባል። “ወጣቶችም ሆናችሁ ትልልቆች በአገልግሎቱ ተደሰቱ” እና “አገልግሎቱን ከፍጻሜ የሚያደርሱ ወጣቶች” በሚል ርዕስ የሚቀርቡትን ንግግሮች የሚያበረታቱ ሆነው እንደምታገኟቸው ምንም ጥርጥር የለውም። በመጪው የወረዳ ስብሰባ ወይም የልዩ ስብሰባ ቀን ላይ ራሳቸውን ለይሖዋ መወሰናቸውን በውኃ ጥምቀት ለማሳየት የሚፈልጉ ሁሉ በተቻለ ፍጥነት ለሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ሊያሳውቁት ይገባል። የልዩ፣ የወረዳና የአውራጃ ስብሰባዎቻችን አንዱ አቢይ ገጽታ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት ነው። የልዩ ስብሰባ ቀን በሚደረግበት ሳምንት የሚጠናውን መጠበቂያ ግንብ ይዛችሁ መምጣት አትርሱ።

አገልግሎታችንን ከፍጻሜ ለማድረስ ስንጥር የግል ጉዳዮቻችንና የምናደርጋቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች ይሖዋ በአደራ የሰጠንን ሥራ የምንሠራበትን ጊዜ እንዳይሻሙብን ጥንቃቄ እናደርጋለን። በዚህ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም አማካኝት የሚቀርብልን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማበረታቻ ሁላችንም ለአገልግሎቱ የምንሰጠውን ተገቢ ትኩረት እንደያዝን ለመቀጠልና አገልግሎቱን በተሟላ ሁኔታ ለመፈጸም ምን ማድረግ እንዳለብን እንድናስተውል ሊረዳን ይገባል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ