መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ሁላችንንም ስለሚያሳስበን አንድ ጉዳይ ከሰዎች ጋር እየተነጋገርን ነበር። በተፈጥሮ ላይ እየደረሰ ያለው ቀውስ ብዙ ሰዎች ምድር ወደፊት ለሰው ልጆች መኖሪያ አትሆንም የሚል መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ አድርጓቸዋል። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም መዝሙር 37:11ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ወደፊት ሁኔታዎች ይሻሻላሉ ብለን እንድናምን የሚያደርጉ አንዳንድ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያቶችን ያብራራል።”
ንቁ! ነሐሴ 2008
“ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ ከሰዎች ጋር አንድ አስፈላጊ ነጥብ እየተወያየን ነው። ብዙ ሰዎች የምድር ሙቀት መጨመር ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሕልውና አደጋ ላይ ይጥላል ብለው ያምናሉ። ይህ ችግር እንዴት ይፈታል ብለው ያስባሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ኢሳይያስ 11:9ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ምድር ለሰው ልጆች መኖሪያ ሆና መቀጠሏ አጠራጣሪ እንዳልሆነ የሚያሳዩ ምክንያቶችን ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“አንድ ጥያቄ ብጠይቅዎት ደስ ይለኛል። ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ላይ የሰጠውን ትእዛዝ መከተሉ በቤተሰብ ውስጥ የበለጠ ደስታ እንዲኖር አስተዋጽዖ ያደርጋል ቢባል ይስማማሉ? [ዮሐንስ 13:34ን አንብብ። መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ ርዕስ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ኢየሱስ ያስተማራቸውን ትምህርቶችና የተወውን ምሳሌ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችል ይገልጻል።” በገጽ 16 እና 17 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ነሐሴ 2008
“የምድር የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከሚያሳስባቸው ሰዎች ጋር እየተነጋገርን ነበር። ሰብዓዊ መንግሥታት የምድር ሙቀት መጨመር ያስከተለውን ችግር በተሳካ ሁኔታ የሚወጡት ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ኤርምያስ 10:23ን አንብብ።] ይህን ርዕስ እንደሚወዱት እርግጠኛ ነኝ። አምላክ በፕላኔታችን ላይ ለተጋረጡት ችግሮች ስለሚያመጣው መፍትሔ ይናገራል።”