መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“አንድ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከግማሽ በላይ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ የሚኖረው በድህነት ነው። ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚቻል ይመስሎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ድህነት ለዘለቄታው እንደሚወገድ የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ይዟል።”—መዝሙር 72:12, 13 እና 16ን አንብብ።
ንቁ! ነሐሴ 2003
“ነፍሳት አደገኛ የሆኑ በሽታዎችን ያስተላልፋሉ። ራሳችንን ለመከላከል ምን ማድረግ እንደምንችል ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ራሳችንን እንዴት መከላከል እንደምንችል የሚናገር ከመሆኑም በላይ መጽሐፍ ቅዱስ ማንኛውም ዓይነት በሽታ ስለሚወገድበት ጊዜ የሚሰጠውን ተስፋ ያብራራል።” ኢሳይያስ 33:24ን በማንበብ ደምድም።
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 15
“አብዛኞቹ ሰዎች ጥሩ ስም ማትረፍ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንዳንዶች ከሞትኩ በኋላ በምን ዓይነት ስም እታወስ ይሆን ብለው ያስባሉ። ስለዚህ ጉዳይ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም መክብብ 7:1ን አንብብ።] ይህ መጠበቂያ ግንብ በሰዎችም ሆነ በአምላክ ዘንድ እንዴት መልካም ስም ማትረፍ እንደምንችል ያብራራል።”
Aug. 8
“ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከአየር ጠባይ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ጉዳት አስከትለዋል። በዚህ ሳቢያ የሚከሰተውን ጉዳት ለመቀነስ ምን ቢደረግ ይሻላል ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት የአየር ጠባይ መለዋወጥ የሚያስከትለውን ችግር እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርበውን መፍትሔ ያብራራል።”—ኢሳይያስ 35:1ን አንብብ።