መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“ብዙዎች ችግር ሲያጋጥማቸው ‘አምላክ በእርግጥ ለሰዎች ያስባል? የሚደርስብንን መከራስ ይመለከታል?’ የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት አምላክ በዛሬው ጊዜ ለእኛ እንደሚያስብልን ያሳየባቸውን መንገዶች እንዲሁም መከራን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ያደረገውን ዝግጅት ይገልጻል።” ዮሐንስ 3:16ን አንብብ።
ንቁ! ሐምሌ 2004
“በዛሬው ጊዜ በርካታ ሰዎች በብቸኝነት ይሰቃያሉ። ብቸኝነት ከሌሎች ሰዎች የመነጠልና የመገለል ስሜት ያሳድራል። ይህ ስሜትን የሚጎዳ ነው ቢባል አይስማሙም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም መዝሙር 25:16ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም ብቸኝነትን ለማሸነፍ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 15
“አብዛኞቹ ሰዎች በዛሬው ጊዜ እንደዚህ ያለ ክንውን [በሽፋኑ ላይ የሚገኘውን ሥዕል አሳየው] እንደተፈጸመ የሚገልጽ ዜና ቢሰሙ ለማመን ይከብዳቸው ይሆናል። እርስዎስ ምን ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ማርቆስ 4:39ን አንብብ።] ኢየሱስ ፈጽሟቸዋል የሚባሉት ተዓምራት እውነተኛ ለመሆናቸው ምን ማስረጃ አለ? ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል።”
Awake! July 22
“በዘመናችን ወንጀለኞች ሰዎችን ለማጭበርበር በየጊዜው የተለያዩ ዘዴዎችን ይቀይሳሉ። ይህ ሁኔታ ያሳስብዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የንቁ! እትም እንዳንጭበረበር ሊረዱን የሚችሉ ጥቂት መሠረታዊ ነጥቦችን ያብራራል።” ምሳሌ 22:3ን አንብብ።