መጽሔቶቻችንን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ብዙ ሰዎች አጉል እምነቶችና ልማዶች ምንም ጉዳት እንደሌላቸው አድርገው ያስባሉ። [ገጽ 5 ላይ ከሚገኘው ሳጥን ውስጥ ከተዘረዘሩት አጉል እምነቶች መካከል አንድ ወይም ሁለቱን አንብብለት።] ከእነዚህ አጉል እምነቶች በስተጀርባ ያለው ማን እንደሆነ አስበው ያውቃሉ? [መልሱን ካዳመጥክ በኋላ 2 ቆሮንቶስ 11:14ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ አጉል እምነትን በተመለከተ ምን እንደሚል ማወቅ እንዲችሉ እባክዎ ይህን መጽሔት ያንብቡ።”
ንቁ! ነሐሴ 2000
“የመጨረሻዎቹ ቀናት አስቸጋሪ እንደሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። [2 ጢሞቴዎስ 3:1, 3ን አንብብ።] በዓለም ዙሪያ የሚፈጸሙት ወንጀሎች የዚህን ትንቢት እውነተኝነት የሚያረጋግጡ ናቸው። ፖሊሶች ባይኖሩ ኖሮ ደግሞ ሁኔታዎቹ ምን ያህል ከዚህ የከፉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገምት። ይህ የንቁ! እትም ፖሊሶች በዓለም ዙሪያ የሚያጋጥማቸውን ፈተናዎች አስመልክቶ ይናገራል።”
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 15
“ከሁሉም በላይ ታማኝ መሆን የሚኖርብን ለማን ነው ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ከሁሉም በላይ ለእውነተኛው አምላክ ታማኝ መሆን እንዳለብን ይናገራል። [ገጽ 5ን አውጣና 2 ሳሙኤል 22:26ን አንብብ።] ለአምላክ ታማኝ መሆናችን በሌሎች ላይ መጥፎ ድርጊት ከመፈጸም እንድንቆጠብ እንደሚያደርገን ያውቃሉ? ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረውን ይህን መጽሔት ቢያነቡ እንደሚደሰቱ እርግጠኛ ነኝ።”
Aug. 22
“ከአካባቢ ብክለት ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሰው ልጅ መፍትሔ ያገኝላቸዋል ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] የችግሩ ዋነኛ መንስኤ አባካኝነት ነው። ኢየሱስ ተከታዮቹ አባካኞች እንዳይሆኑ አስተምሯቸዋል። [ዮሐንስ 6:12ን አንብብ።] የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያ መከተል ቤተሰቦች የመጣል አባዜ የተጠናወተውን ኅብረተሰብ እንዳይመስሉ እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል ይህ መጽሔት ያሳያል።”