መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ኢየሱስ በተናገረው በዚህ ሐሳብ ላይ ያለዎትን አመለካከት ባውቅ ደስ ይለኛል። [ማቴዎስ 5:3ን አንብብ።] ደስታ ለማግኘት መንፈሳዊነት አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት፣ መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ መንፈሳዊነትን እንዲሁም መንፈሳዊ ሰዎች መሆን የምንችልበትን መንገድ በተመለከተ ምን እንደሚል የሚገልጽ ጠቃሚ ሐሳብ ይዟል።”
ንቁ! ነሐሴ 2007
አንድ ወጣት ስታገኝ እንዲህ ልትል ትችላለህ:- “በአንተ ዕድሜ ያሉ በርካታ ልጆች ሰዎች በተንኮል ተነሳስተው ባወሩባቸው ሐሜት ተጎድተዋል። አንተስ እንዲህ ዓይነት ነገር ደርሶብሃል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ ሐሜት የተወራባቸው ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ የሚገልጽ ጠቃሚ ምክር ይሰጣል። ከዚህም በተጨማሪ ሐሜትን ከማሰራጨት እንዴት መቆጠብ እንደምንችል ይገልጻል።” ገጽ 12 ላይ ያለውን ርዕስ አሳየውና በርዕሱ ውስጥ ከሚገኙት ጥቅሶች አንዱን አንብብ።
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 15
“በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በተመለከተ ምን አመለካከት እንዳለዎት ባውቅ ደስ ይለኛል። [ዕብራውያን 3:4ን አንብብ።] ይህ አጽናፈ ዓለም ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ ያለው ንድፍ አውጪ አለው ቢባል ይስማማሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ፈጣሪ አለ ብሎ ማመን ከእውነተኛ ሳይንስ ጋር ይስማማ እንደሆነና እንዳልሆነ ያብራራል።”
ንቁ! መስከረም 2007
“አብዛኞቻችን ጥሩ ጤንነትና ረጅም ዕድሜ እንዲኖረን እንፈልጋለን። ምንጊዜም ብሩሕ አመለካከት መያዝ ጤንነታችንን ሊያሻሽል እንደሚችል ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ምሳሌ 17:22ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ብሩሕ አመለካከት ማዳበር ያለውን ጥቅም ያብራራል።” ገጽ 26 ላይ ያለውን ርዕስ አሳየው።