መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“በዛሬው ጊዜ ሰዎች ሌሎችን ሲበድሉና ሲያንገላቱ ማየት በጣም የተለመደ ነው። ኢየሱስ የተናገራቸውን እነዚህን ቃላት በተግባር ላይ የሚያውሉ ብዙ ሰዎች ቢኖሩ ኖሮ ሁኔታዎች የሚለወጡ ይመስልዎታል? [ማቴዎስ 7:12ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት የሰው ልጆች ክብር አግኝተው መሠረታዊ መብታቸው የሚጠበቀው እንዴት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ይዟል።”
ንቁ! ነሐሴ 2006
“በሞት ያጣናቸውን ሰዎች እንደገና የምናይበት ጊዜ ይመጣል ብለው አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] እስቲ ኢየሱስ ስለ ሙታን የሰጠውን ተስፋ ይመልከቱ። [ዮሐንስ 5:28, 29ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ስንሞት ምን እንደምንሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ያብራራል።” በገጽ 28 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 15
“ኢየሱስ ስለተናገረው አንድ ሐሳብ ምን እንደሚሰማዎት ብናውቅ ደስ ይለናል። [ማቴዎስ 5:5ን አንብብ።] ይህ ተስፋ ፍጻሜውን በሚያገኝበት ጊዜ፣ በአሁን ሰዓት በምድር ላይ ያሉት ሁኔታዎች እንዲሁ የሚቀጥሉ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት፣ ኢየሱስ ምድርን እንዴት እንደሚለውጣት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ይገልጻል። ከዚህም በላይ ምድርን የሚወርሱት እነማን እንደሆኑ ያብራራል።”
ንቁ! መስከረም 2006
“ብዙ ሰዎች በአምላክ ማመን ሳይንሳዊ ድጋፍ ያለው ስለመሆኑ እርግጠኞች አይደሉም። እርስዎስ ምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ዕብራውያን 3:4ን አንብብ።] ይህ የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም አንዳንድ ሳይንቲስቶች በፈጣሪ መኖር እንዲያምኑ ያደረጋቸውን አሳማኝ ማስረጃ ይዟል።”