‘ለምሥራቹ ስትሉ ሁሉን ነገር አድርጉ’
1. የምሥራቹ ሰባኪዎች ምን ለማድረግ ፈቃደኞች ናቸው? ለምንስ?
1 ሐዋርያው ጳውሎስ ምሥራቹን ለሌሎች የመስበክ ግዴታ እንደተጣለበት ይሰማው ነበር። (1 ቆሮ. 9:16, 19, 23) እኛም በተመሳሳይ የሰዎች ዘላቂ ደኅንነት ስለሚያሳስበን ምሥራቹን ለመናገር የተቻለንን ጥረት ሁሉ እናደርጋለን።
2. በስብከቱ ሥራ ላይ ስንሳተፍ ምን ማስተካከያዎችን ለማድረግ ፈቃደኞች መሆን አለብን? ለምንስ?
2 ሰዎች በሚገኙበት ቦታና ሰዓት ስበኩ፦ አንድ ጎበዝ ዓሣ አጥማጅ መንጠቆውን ወይም መረቡን የሚጥለው ዓሦች ሊገኙ በሚችሉበት ጊዜና ቦታ ላይ እንጂ እሱ ባሰኘው ጊዜና ደስ ባለው ቦታ አይደለም። እኛም ‘ሰዎችን የምናጠምድ’ እንደመሆናችን መጠን በክልላችን ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች ለማግኘት በፕሮግራማችን ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎችን ማድረግ ያስፈልገን ይሆናል። እንዲህ ማድረጋችን ‘የተለያዩ ዓይነት ዓሦችን’ ለመሰብሰብ ከሚደረገው ልዩ ሥራ የበለጠ ደስታ ለማግኘት ያስችለናል። (ማቴ. 4:19፤ 13:47) ሰዎችን ቤታቸው ለማግኘት አመሻሹ ላይ ከቤት ወደ ቤት ማገልገል ወይም ማለዳ በመንገድ ላይ መመሥከር እንችላለን? ጳውሎስ ‘ምሥራቹን በሚገባ የመመሥከር’ ዓላማ የነበረው ሲሆን ይህን ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያገኛቸውን አጋጣሚዎች ሁሉ ጥሩ አድርጎ ይጠቀምባቸው ነበር።—ሥራ 17:17፤ 20:20, 24
3, 4. በአገልግሎት ላይ አቀራረባችንን እንደየሁኔታው መቀያየር የምንችለው እንዴት ነው? ይህስ ምን ውጤት ያስገኛል?
3 አቀራረባችሁን እንደየሁኔታው ቀያይሩ፦ ዓሣ አጥማጆች የሚፈልጉትን ዓይነት ዓሣ ለማጥመድ ሲሉ ዘዴያቸውን በየጊዜው ይቀያይራሉ። እኛስ የመንግሥቱን ምሥራች በክልላችን የሚኖሩ ሰዎችን በሚማርክ መንገድ መስበክ የምንችለው እንዴት ነው? ብዙ ሰዎች የሚያሳስባቸውን አንድ ርዕሰ ጉዳይ በዘዴ ካነሳን በኋላ ሰዎቹ ስለ ጉዳዩ የሚሰጡትን ሐሳብ በጥሞና ማዳመጥ ይኖርብናል። (ያዕ. 1:19) በልባቸው ውስጥ ያለውን ለማወቅ የአመለካከት ጥያቄ ልንጠይቃቸው እንችላለን። (ምሳሌ 20:5) እንዲህ ማድረጋችን አቀራረባችንን ለመለዋወጥና ምሥራቹን ልባቸውን በሚነካ መንገድ ለመስበክ ያስችለናል። ጳውሎስ “ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ሁሉንም ነገር” ሆኗል። (1 ቆሮ. 9:22) የሰዎችን ልብ ለመንካት ቁልፉ ነገር አቀራረባችንን እንደየሁኔታው መለዋወጥ ነው።
4 ለሰዎች ‘መልካም ዜና በማብሰሩ’ ሥራ መካፈል እንዴት ያለ አስደሳች መብት ነው! (ኢሳ. 52:7) እንግዲያው ምሥራቹን በተቻለን መጠን ለብዙ ሰዎች ‘ለማካፈል ስንል ሁሉን ነገር እናደርግ።’—1 ቆሮ. 9:23