የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የተባለውን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት ሌላ መንገድ
በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሰዎች፣ በተለይ ደግሞ ከክርስትና ሃይማኖት ውጭ ያሉት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የላቸውም። አንዳንድ አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ሲያስጠኑ ጥናታቸው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋት የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የተባለውን ብሮሹር ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ወንድም ከጥናቱ ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ላይ ሲደርሱ ከብሮሹሩ ላይ ክፍል 1ን ያወያየዋል። ከዚያም ከእያንዳንዱ ጥናት በኋላ ከብሮሹሩ ላይ አንድ ክፍል ይወያያሉ። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መጠነኛ እውቀት ካለው አሊያም ጭራሽ እውቀት ከሌለው ሰው ጋር እያጠናህ ነው? ‘ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ እንዲያገኝ የሚያስችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍት’ እንዲማር ለመርዳት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ከማስጠናት በተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የተባለውን ብሮሹር ማወያየት ትችላለህ።—2 ጢሞ. 3:15