የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“በዚህ ወቅት ብዙ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ያስባሉ። በእርስዎ አመለካከት፣ ኢየሱስ ያከናወነው ትልቁ ሥራ ምንድን ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ በገጽ 16 ላይ የሚገኘውን ይህን ርዕስ ይመልከቱ።” የታኅሣሥ 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና ከንዑስ ርዕሶቹ መካከል በአንዱ ላይ ተወያዩ። በተጨማሪም በንዑስ ርዕሱ ውስጥ ከሚገኙት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አንብቡ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ ከቀሪዎቹ ጥያቄዎች መካከል በአንዱ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“በገና ወቅት ብዙዎች የጽድቅ ሥራ መሥራት ያስደስታቸዋል። ከእነዚህ መካከል እርስዎ ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ለየትኛው ነው? [በገጽ 3 ላይ ያሉትን ዝርዝሮች አሳየውና ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም የመረጠውን ሐሳብ የሚያብራራውን ርዕስ ገልጠህ፣ ለዚያ የተመረጠውን ጥቅስ አንብብ።] ይህ መጽሔት በገና በዓል ወቅት ብቻ ሳይሆን ዓመቱን ሙሉ ኢየሱስን እንዴት ማሰብ እንደምንችል የሚጠቁሙ ነጥቦችን ይዟል።”
ንቁ! ታኅሣሥ
“ብዙ ሰዎች በሚደርስባቸው ጫና የተነሳ እንደሚጨነቁ የታወቀ ነው። አሁን አሁን ሰዎች ትዕግሥት እያጡ እንደመጡ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ አስጨናቂ ዘመን እንደሚመጣ የተናገረው ትንቢት እየተፈጸመ እንደሆነ ይሰማቸዋል። [2 ጢሞቴዎስ 3:1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ትዕግሥት ማጣት ጎጂ የሆነው ለምን እንደሆነና ትዕግሥትን ማዳበር የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”