የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ዛሬ የመጣነው ለቤተሰብ ሕይወት ጠቃሚ የሆነ ሐሳብ ልናካፍልዎት ነው። ብዙ ወላጆች፣ ልጆቻቸው አምላክን የሚወዱ እንዲሆኑ ይፈልጋሉ። ግን ወላጆች ልጆቻቸው አምላክን የሚወዱ እንዲሆኑ ማስተማር የሚችሉ ይመስልዎታል? ወይስ ልጆች ይህን ማድረግ ያለባቸው በራሳቸው ጥረት ነው?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። በታኅሣሥ 1 መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን የመጀመሪያ ጥያቄ አሳየው፤ ከዚያም በጥያቄው ሥር ባለው ሐሳብ እና በአንቀጹ ላይ ካሉት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“ከሰዎች ጋር ስለ አምላክ እየተነጋገርን ነበር። ሁሉም ሰው ስለ አምላክ የራሱ የሆነ አመለካከት እንደሚኖረው የታወቀ ነው። ብዙ ሰዎች አምላክን እንዴት አድርገው የሚመለከቱት ይመስልዎታል? የራሱ የሆነ አካል የሌለው ኃይል እንደሆነ አድርገው ነው? ወይስ በግለሰብ ደረጃ ስለ እነሱ የሚያስብ ወዳጅ እንደሆነ ይሰማቸዋል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ከእሱ ጋር ምን ዓይነት ዝምድና እንዲኖረን እንደሚፈልግ ይናገራል። [ያዕቆብ 4:8ሀን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ ከአምላክ ጋር ለመቀራረብ ከፈለግን ልናደርጋቸው የሚገቡ ሦስት ነገሮችን ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ
“የመጣነው እየተስፋፋ በሄደ አንድ አሳሳቢ የጤና ችግር ላይ ለመወያየት ነው። የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው ከአራት ሰዎች አንዱ በሆነ ወቅት ላይ እንደ መንፈስ ጭንቀት ባሉ የአእምሮ ሕመሞች ይጠቃል። የአእምሮ ሕመም ይበልጥ እየተስፋፋ እንደመጣ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወደፊት በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ከበሽታም ሆነ ከሥቃይ ነፃ የሚሆኑበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል። [ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ከአእምሮ ሕመሞች ጋር በተያያዘ ሁላችንም ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮችን ያብራራል።”