ማቋረጥ አለባችሁ?
አንዳንድ አስፋፊዎች በመስክ አገልግሎት ሲካፈሉ የተወሰነ ሰዓት ላይ አገልግሎት የማቆም ልማድ አላቸው፤ ምናልባትም እንዲህ የሚያደርጉት እኩለ ቀን ላይ ሊሆን ይችላል። እርግጥ አንዳንድ አስፋፊዎች ያሉበት ሁኔታ አገልግሎታቸውን በተወሰነ ሰዓት እንዲያቆሙ ያስገድዳቸዋል። ይሁንና አብረዋችሁ የተመደቡት አስፋፊዎች አገልግሎት ስለጨረሱ ወይም በአካባቢው የተለመደ ስለሆነ ብቻ የተወሰነ ሰዓት ላይ አገልግሎታችሁን ታቋርጣላችሁ? በስብከቱ ሥራ የምታደርጉትን ተሳትፎ ለጥቂት ደቂቃዎች በማራዘም በመንገድ ላይ እንደመመሥከር ባሉ የአደባባይ ምሥክርነት ዘርፎች መካፈል ትችላላችሁ? ወደ ቤት ስትመለሱ አንድ ወይም ሁለት ተመላልሶ መጠየቆችን ማድረግ ትችላላችሁ? ፍላጎት ያሳየን አንድ ሰው ቤቱ ሄዳችሁ ብታናግሩት አሊያም ለአንድ ሰው መጽሔቶችን ብታበረክቱ እንኳ ምን ያህል ሥራ እንዳከናወናችሁ መገመት ትችላላችሁ! አገልግሎት ማቋረጥ ከሌለብን፣ በስብከቱ ሥራ የምናሳልፈውን ጊዜ በጥቂት ደቂቃዎች በማራዘም ለይሖዋ የምናቀርበውን “የምስጋና መሥዋዕት” ማሳደግ እንችላለን።—ዕብ. 13:15