የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/13 ገጽ 4-6
  • ተሞክሮዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተሞክሮዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ለሌሎች ልባዊ ኣሳቢነት በማሳየት ይሖዋን ምሰል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • በብሮሹሮች ተጠቅማችሁ የመንግሥቱን ምሥራች አውጁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • አዲስ የሚበረከት ብሮሹር!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
km 12/13 ገጽ 4-6

ተሞክሮዎች

◼ አውስትራሊያ፦ ጆን የተባለ አንድ የተማረ ሰው በልጅነቱ ቤተ ክርስቲያን ይሄድ ነበር፤ በኋላ ግን አምላክ የለም የሚለው ጽንሰ ሐሳብ “ቀንደኛ ደጋፊ” ሆነ። አንድ አቅኚ ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው? የተባለውን ብሮሹር ሰጠው፤ በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ የሕይወት አመጣጥ የተባለውን ብሮሹር ይዞለት መጣ። አቅኚው አዳዲስ መጽሔቶችን ለሰውየው መውሰዱን የቀጠለ ሲሆን ከመጽሔቶቹ ላይ ስለ ፍጥረት ወይም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የሚናገሩ ርዕሶችን ያሳየው ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? የተባለውን መጽሐፍ ለጆን ቢሰጠው እንደሚቀበለው ስለተሰማው ይህን መጽሐፍ አመጣለት። ጆን መጽሐፉን ካነበበው በኋላ አምላክ የለም የሚለው አቋሙ “መለሳለሱን” ተናገረ። ከዚያም አቅኚው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ሰጠውና ገጽ 20 አንቀጽ 8 እንዲሁም ገጽ 23-24 ከአንቀጽ 13-16 ላይ ያሉትን ሐሳቦች አሳየው። ጆን በመጽሐፉ ላይ ያሉት ጥቅሶች በጣም ስለ ነኩት “መጽሐፍ ቅዱስን እንደገና መመርመር ሳይኖርብኝ አይቀርም” በማለት ተናግሯል።

◼ ሜክሲኮ፦ አንድ ሰው፣ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በአምላክ መንፈስ መሪነት መሆኑን እንደማያምን ለአንድ አስፋፊ ነገረው። አስፋፊውም መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ መሪነት መጻፉን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ማየት ይፈልግ እንደሆነ ጠየቀው። ለተወሰነ ጊዜ ከተወያዩ በኋላ ሰውየው ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሚማረው ነገር ልቡ ተነካ። በተለይ አምላክ ስላወጣቸው መመሪያዎች ማወቁ ልቡን ነክቶታል። አስፋፊውን እንዲህ አለው፦ “መጀመሪያ ላይ እኔና አንተ መጽሐፍ ቅዱስን አብረን ስናነብ፣ ምክር እንደሚሰጡ ሌሎች መጽሐፎች አድርጌ ስላሰብኩት ሐሳቡ ብዙም አልነካኝም። አሁን ስናነበው ግን በተለይ ደግሞ ሥነ ምግባርን አስመልክቶ የሚሰጠውን ምክር ስመለከት ሕሊናዬ እየወቀሰኝ ነው።”

◼ ዩናይትድ ስቴትስ፦ ሕዝብ በሚበዛባቸው ትላልቅ ከተሞች በሚሰጥ ልዩ ምሥክርነት ላይ የተካፈሉ አንድ ባልና ሚስት፣ ከታይዋን የመጣች አንዲት ሴት አገኙ፤ ሴትየዋ በአምላክ ብታምንም መጽሐፍ ቅዱስ የምዕራባውያን መጽሐፍ ነው የሚል እምነት ነበራት። ይህች ሴት የተመቻቸ ሕይወት ቢኖራትም የሕይወት ዓላማ ምን እንደሆነ ግራ ገብቷት ነበር። ወደ ጽሑፍ መደርደሪያው የመጣችው መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ሊረዳት እንደሚችል ተስፋ በማድረግ ነበር። ባልና ሚስቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ እና ላስቲንግ ፒስ ኤንድ ሃፒነስ—ሃው ቱ አቴይን ኢት የተባለውን ብሮሹር በመጠቀም ጥናት አስጀመሯት። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከተባለው መጽሐፍ ላይ ምዕራፍ 2⁠ን ከማስጠናት ይልቅ “ለመላው የሰው ዘር በረከት የሚያስገኝ መመሪያ የያዘ መጽሐፍ” የሚለውን የብሮሹሩን ክፍል ተጠቅመው አወያዩዋት። በዚህ ክፍል ውስጥ ያሉትን የመጀመሪያዎቹን ስድስት አንቀጾች እንደተወያዩ ሴትየዋ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ሃይማኖታዊ ጽሑፎች በጣም የተለየ እንደሆነ በአድናቆት ተናገረች። ፍጻሜያቸውን ስላገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ከተወያዩ በኋላ ደግሞ እንዲህ አለች፦ “የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ትክክል ነው ብዬ የማስበው ሌላ መጽሐፍ የለም!”

◼ ጃፓን፦ አንድ አስፋፊ የሚያነጋግረው ሰው በአምላክ እንደማያምን ቢነግረውም አልፎ አልፎ እየመጣ በንቁ! መጽሔት ላይ የሚወጣውን “ንድፍ አውጪ አለው?” የሚለውን ርዕስ በአጭሩ ማወያየቱን ቀጠለ። ቀስ በቀስ ሰውየው አመለካከቱን ቀይሮ ‘አምላክ ሳይኖር አይቀርም’ ማለት ጀመረ። አሁን ይህ ሰው በአምላክ መኖር የሚያምን ሲሆን ከአስፋፊው ጋር ከአምላክ የመጣ ምሥራች! የተባለውን ብሮሹር ያጠናል።

◼ ካናዳ፦ አንዲት እህት፣ ከቤቷ ወጥታ ወደ መኪናዋ እየሄደች ላለች አንዲት ሴት በቅርብ የወጡ መጽሔቶችን አበረከተችላት። ያበረከተችላት እህት ተመልሳ መጥታ ስትጠይቃት ግን ሴትየዋ ለመወያየት ፍላጎት እንደሌላትና በአምላክ እንደማታምን ፈርጠም ብላ ነገረቻት። እህት ግን ተስፋ ሳትቆርጥ ኤ ሳቲስፋይንግ ላይፍ—ሃው ቱ አቴይን ኢት የተባለውን ብሮሹር ይዛላት መጣች። እህት ሴትዮዋን ቤቷ ስታገኛት፣ በአምላክ እንደማታምን የምታውቅ ቢሆንም እንኳ ነጠላ ወላጅ መሆኗን ስለተገነዘበች ስለ እሷ ማሰቧን እንዳላቆመች ነገረቻት። ከዚያም ብሮሹሩን አውጥታ ጥሩ ምክር ማግኘት የሚቻለው ከየት እንደሆነ የሚናገረውን ገጽ 4 አንቀጽ 6 ላይ ያለውን ሐሳብ ከሴትዮዋ ጋር ተወያዩበት። እንዲሁም ልጆችን ስለማሳደግ የሚናገረውን ትምህርት 2⁠ን እንድታነብበው አበረታታቻት። ሴትዮዋም ብሮሹሩን በደስታ ተቀበለቻት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ