jw.orgን በአገልግሎታችሁ ላይ ተጠቀሙበት—“የይሖዋ ወዳጅ ሁን”
jw.org ላይ በሚገኘው “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች” በሚለው ታብ ሥር “የይሖዋ ወዳጅ ሁን” የሚል ለልጆች የተዘጋጀ ክፍል አለ፤ በዚህ ክፍል ውስጥ መዝሙሮች፣ ቪዲዮዎችና መልመጃዎች ይገኛሉ። ይህን ክፍል በአገልግሎታችሁ ተጠቅማችሁበት ታውቃላችሁ? ትናንሽ ልጆች ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ካላችሁ ይህን ክፍል ለምን አታሳዩትም? እንዲህ ማድረጋችሁ ድረ ገጻችን ላይ የሚገኙትን ሌሎች ነገሮች እንዲመለከት ሊያነሳሳው ይችላል።
አንድ ወንድም የመንግሥት ዜና ቁ. 38ን ሲያሰራጭ አንዲት ሴት አገኘ፤ ሴትየዋም ትራክቱን እንደሰጣት ማንበብ ጀመረች። የሴትየዋ ትናንሽ ልጆች ስለ ትራክቱ ለማወቅ ጉጉት አደረባቸው። ወንድም የትራክቱን ይዘት በአጭሩ ከገለጸ በኋላ ከትራክቱ ጀርባ ላይ ያለውን የድረ ገጹን አድራሻ አሳያት። ሴትየዋ ፍላጎት ስላሳየች ወንድም በሞባይሉ ተጠቅሞ ለእሷና ለልጆቿ ከካሌብ ቪዲዮዎች መካከል አንዱን አሳያቸው።
አንዲት እህት፣ ትናንሽ ልጆች ላሏት የሥራ ባልደረባዋ ስለ ድረ ገጻችንና ድረ ገጹ ቤተሰብን አስመልክቶ ስለያዛቸው መረጃዎች ነገረቻት። ሴትየዋም jw.org የተባለውን ድረ ገጽ ከልጆቿ ጋር ተመለከተች። ከዚያም ልጆቿ ቤት ውስጥ ወዲያ ወዲህ የሚሉት “የይሖዋ ወዳጅ ሁን” በሚለው ክፍል ውስጥ የሚገኘውን “ቃሉን ስበክ” የተባለውን መዝሙር እየዘመሩ እንደሆነ ለእህት ነገረቻት።
በjw.org ላይ ከሚገኘው ከዚህ ክፍል ጋር በደንብ ተዋወቅ፤ ከዚያም የፈለግከውን ቪዲዮ፣ መዝሙር ወይም መልመጃ ሞባይልህ ላይ ጫን። እንዲህ ካደረግክ ይህንን የjw.org ገጽታ አገልግሎት ላይ መጠቀም ትችላለህ። ይህ የድረ ገጹ ክፍል ጌታን ለማገልገል የሚረዳን እንዴት ያለ ግሩም መሣሪያ ነው።—ሥራ 20:19