በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—በኢንተርኮም መመሥከር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በኢንተርኮም መመሥከር ሊያስፈራ ይችላል። ታዲያ ይህ ተፈታታኝ ሁኔታ ለመልካም ሥራ ያለንን ቅንዓት እንዳያቀዘቅዝብን ምን ማድረግ እንችላለን? አንዳንድ ሰዎች ምሥራቹ ሊደርሳቸው የሚችለው በኢንተርኮም አማካኝነት በሚሰጥ ምሥክርነት ብቻ ሊሆን እንደሚችል ማስታወሳችን ጠቃሚ ነው። (ሮም 10:14) በዚህ ዘዴ ውጤታማ ምሥክርነት መስጠት እንደሚቻል ተሞክሮዎች ያሳያሉ። (የ2011 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 65-66ን እና የ2000 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 54 አን. 3ን ተመልከት።) እስቲ ቀጥሎ የቀረቡትን ሐሳቦች እንመልከት።
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
በቤተሰብ አምልኳችሁ ወቅት በኢንተርኮም በምትመሠክሩበት ጊዜ እንደምታደርጉት ሳይተያዩ ማውራትን ተለማመዱ።