ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—በካሜራ ወይም በኢንተርኮም አማካኝነት መመሥከር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የቴክኖሎጂ እድገትና የወንጀል መበራከት ብዙ ሰዎች የደህንነት ካሜራና የኢንተርኮም ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል። እኛ ሳናየው እሱ ግን እያየን ላለ ሰው ምሥራቹን መስበክ ሊያስፈራን ይችላል። የሚከተሉት ማሳሰቢያዎች በካሜራ ወይም በኢንተርኮም አማካኝነት ስንመሠክር ይበልጥ ድፍረት እንዲኖረን ይረዱናል።
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
አዎንታዊ ሁኑ። ቤታቸው ካሜራ ወይም ኢንተርኮም ያላቸው ብዙ ሰዎች እኛን ለማነጋገር ፈቃደኛ ናቸው
አንዳንድ ካሜራዎች ደወሉን ከመጫናችሁም በፊት መቅረጽ እንደሚጀምሩ እንዲሁም የቤቱ ባለቤት ወደ በሩ ስትጠጉ ጀምሮ ሊያያችሁና ሊሰማችሁ እንደሚችል አስታውሱ
በኢንተርኮሙ ስታወሩ ወይም ካሜራውን እየተመለከታችሁ ስትናገሩ ግለሰቡን በአካል እንደምታነጋግሩት አድርጋችሁ ተናገሩ። ፈገግ ብላችሁ እንዲሁም አካላዊ መግለጫዎችን እየተጠቀማችሁ ተናገሩ። ግለሰቡ በአካል ቢመጣ ልትነግሩት ያሰባችሁትን ነገር ንገሩት። ካሜራ ካለ ፊታችሁን ወደ ካሜራው በጣም አታስጠጉ። ደወል ስትደውሉ መልስ ካላገኛችሁ ምንም መልእክት አትተዉ
ውይይታችሁን ከጨረሳችሁ በኋላም የቤቱ ባለቤት ሊያያችሁ ወይም ሊሰማችሁ እንደሚችል አትዘንጉ