የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/15 ገጽ 4
  • የአቀራረብ ናሙናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቀራረብ ናሙናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
km 2/15 ገጽ 4

የአቀራረብ ናሙናዎች

ለመታሰቢያው በዓል መጋበዣ

“ሰዎች መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሚያዝያ 3 ቀን 2015) በሚከበር አንድ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ የጥሪ ወረቀት እየሰጠን ነው። በዚህ ዕለት በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ይሰበሰባሉ፤ በዚያ ቀን ከኢየሱስ ሞት ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ የሚያብራራ ንግግር ይቀርባል። ይህ የጥሪ ወረቀት ስብሰባው በአካባቢያችን የሚደረገው የትና በስንት ሰዓት እንደሆነ ይገልጻል።”

መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1

“መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሚያዝያ 3 ቀን 2015) የኢየሱስ ክርስቶስ የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ዕለት ነው። በአካባቢያችን የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች ይህን ቀን ያከብራሉ፤ ሌሎች ግን የኢየሱስ ሞት ይህን ያህል ትልቅ ቦታ ሊሰጠው እንደሚገባ አይሰማቸውም። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? ኢየሱስ መሞቱም ሆነ ትንሣኤ ማግኘቱ እኛን የሚጠቅመን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የአምላክ ቃል ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል እንመልከት። [1 ቆሮንቶስ 15:22, 26⁠ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ወደፊት የሚያስገኘውን ጥቅም ይኸውም በዚህች ምድር ማንም ሰው የማይሞትበት ጊዜ እንደሚመጣ ያብራራል።”

ንቁ! መጋቢት

“በቅርቡ በወጣው ንቁ! መጽሔት ላይ ከጎረቤቶቻችን ጋር አጠር ያለ ውይይት እያደረግን ነበር። [የመጽሔቱን ሽፋን አሳየው።] ሁሉም ሰው ‘አምላክ አለ?’ የሚለውን ይህን ጥያቄ አስመልክቶ የራሱ የሆነ አመለካከት አለው። በእርስዎ አስተሳሰብ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው በአምላክ መኖር የሚያምኑ ናቸው ወይስ የማያምኑ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ ለብዙዎች ተስፋ የፈነጠቀ አንድ ጥቅስ ላንብብልዎት። [መዝሙር 37:10, 11⁠ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አራት ማስረጃዎችን ያብራራል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ