የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/14 ገጽ 4
  • የአቀራረብ ናሙናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቀራረብ ናሙናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
km 3/14 ገጽ 4

የአቀራረብ ናሙናዎች

ለመታሰቢያው በዓል መጋበዣ

“ሰዎች ሚያዝያ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሚያዝያ 14 ቀን 2014) በሚከበር አንድ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ የጥሪ ወረቀት እየሰጠን ነው። በዚህ ዕለት በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ይሰበሰባሉ፤ በዕለቱ፣ ከኢየሱስ ሞት ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ የሚያብራራ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ንግግር ይቀርባል። ይህ የጥሪ ወረቀት ስብሰባው በአካባቢያችን የሚደረገው የትና በስንት ሰዓት እንደሆነ ይገልጻል።”

መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1

“ዛሬ የመጣነው አብዛኞቹ ሰዎች በሚያደርጉት አንድ ነገር ላይ ለመወያየት ነው። ሃይማኖታችን ምንም ይሁን ምን ብዙዎቻችን ጸሎት እናቀርባለን። ግን አምላክ ለጸሎታችን መልስ የሚሰጥ ይመስልዎታል? ወይስ የምንጸልየው እንዲሁ ችግራችንን ተናግረን ተንፈስ ለማለት ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት ምን እንደሚል ላሳይዎት። [1 ዮሐንስ 5:14⁠ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ጸሎት የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”

ንቁ! ሚያዝያ

“ዛሬ የመጣነው በአሁኑ ጊዜ በጣም እየተለመደ ለመጣ አንድ አሳሳቢ ችግር መፍትሔ የሚሆን ሐሳብ ልንነግርዎት ነው። አንዳንድ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ራሳቸውን ለማጥፋት ያስባሉ። አንድ በጭንቀት የተዋጠ ሰው ራሱን ለማጥፋት የሚሞክረው መሞት ስለፈለገ ይመስልዎታል? ወይስ ከችግሩ ለመገላገል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙዎች ብሩህ አመለካከት እንዲኖራቸው የረዳ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኝ አንድ ተስፋ ባሳይዎት ደስ ይለኛል። [ራእይ 21:3, 4⁠ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ አንድ ሰው ችግሮች ቢያጋጥሙትም ራሱን ማጥፋት የሌለበት ለምን እንደሆነ ሦስት ግሩም ምክንያቶችን ይጠቅሳል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ