የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/14 ገጽ 4
  • የአቀራረብ ናሙናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቀራረብ ናሙናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
km 2/14 ገጽ 4

የአቀራረብ ናሙናዎች

በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ

“ዛሬ የመጣነው ሚያዝያ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ስለሚደረግ አንድ ዝግጅት ልንነግርዎት ነው። ይህ ቀን የኢየሱስ ሞት የሚከበርበት ዕለት ነው። አንዳንዶች የኢየሱስ ሞት አስፈላጊ እንደሆነ ስለሚሰማቸው በዚህ ዕለት መታሰቢያውን ያከብራሉ። ሌሎች ደግሞ የኢየሱስ ሞት ጥቅም አለው ብለው አያስቡም። እርስዎ ምን ይላሉ? የኢየሱስ ሞት ለእኔም ሆነ ለእርስዎ የሚያስገኘው ጥቅም ያለ ይመስልዎታል?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። የመጋቢት 1⁠ን መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ አሳየው፤ ከዚያም በመጀመሪያው ጥያቄ ሥር ባለው ሐሳብ እና በዚያ ውስጥ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።

መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1

“ብዙ ሰዎች ‘አምላክ በዓለም ላይ የሚታየውን ግፍ እና መከራ የማያስወግደው ለምንድን ነው?’ የሚለው ጉዳይ ያስጨንቃቸዋል። ምክንያቱ ምንድን ነው ይላሉ? አምላክ ግድ ስለማይሰጠው ወይም የሰው ልጆች ላይ መከራ መድረሱ ተገቢ እንደሆነ ስለሚሰማው ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ዮሐንስ 3:16⁠ን አንብብ።] ብዙዎች ይህ ጥቅስ የአምላክን ደግነት የሚያሳይ እንደሆነ ቢሰማቸውም አምላክ ልጁ እንዲሞት ማድረጉ እነሱን የሚጠቅማቸው እንዴት እንደሆነ የሚያውቁት ነገር የለም። ይህ መጽሔት፣ የኢየሱስ ሞት በምድራችን ላይ የሚታየውን ግፍና መከራ ለማስወገድ በር የሚከፍተው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”

ንቁ! መጋቢት

“ብዙ ሰዎች በዘፍጥረት 1:1 ላይ የሚገኘውን ጥቅስ በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። [ጥቅሱን አንብብ።] አንዳንዶች ይህ ጥቅስ እንደሚናገረው ጽንፈ ዓለማት የተገኙት በፍጥረት መሆኑን ያምናሉ፤ ሌሎች ደግሞ እንደዚህ አይሰማቸውም። እርስዎ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች፣ በዓለማችን ላይ የሚገኙት ነገሮች በፍጥረት እንደመጡ ማመን ይከብዳቸዋል። ለዚህ ምክንያቱ የሃይማኖት መሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛ ትምህርት ስለማያስተምሩ ነው። ይህ መጽሔት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጽንፈ ዓለማት አጀማመር የሚናገረውን አሳማኝና ትክክለኛ ማብራሪያ ይዟል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ