በአዘርባጃን ያሉ አስፋፊዎች ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ሲያበረክቱ
የመግቢያ ናሙናዎች
ንቁ!
ጥያቄ፦ ጊዜያችንን በአግባቡ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?
ጥቅስ፦ መክ 4:6
አበርክት፦ ይህ ንቁ! መጽሔት ቅድሚያ ልንሰጣቸው ከሚገቡ ነገሮች ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል።
እውነትን አስተምሩ
ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
ጥያቄ፦ ምሥራች ማግኘት የምንችለው ከየት ይመስልሃል? [ምሥራች መስማት ትፈልጋለህ? የተባለውን ቪዲዮ አሳይ።]
ጥቅስ፦ ኢሳ 52:7
አበርክት፦ ይህ ብሮሹር ‘የተሻለ ነገር እንደሚመጣ የሚያበስር’ ምሥራች ይዟል፤ ምክንያቱም የያዘው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን መልእክት ነው።
የራስህን መግቢያ አዘጋጅ
ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።