ክርስቲያናዊ ሕይወት
ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር የተባለውን ቡክሌት በአግባቡ እየተጠቀማችሁበት ነው?
ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር በተባለው ቡክሌት ላይ የሚገኘውን ለዕለቱ የተዘጋጀውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስና የመጠበቂያ ግንብ ሐሳብ በየቀኑ የማንበብ ልማድ አላችሁ? ካልሆነ ለምን እንዲህ ለማድረግ ግብ አታወጡም? ብዙዎች የዕለቱን ጥቅስ የሚያነብቡት ጠዋት ላይ ነው። ይህም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ሲያደርጉ በዚያ ላይ እንዲያሰላስሉ ይረዳቸዋል። (ኢያሱ 1:8፤ መዝ 119:97) ከዕለቱ ጥቅስ ይበልጥ ጥቅም ማግኘት የምትችሉት እንዴት ነው? ስለ ጥቅሱ የተሟላ መረጃ ለማግኘት የጥቅሱን አውድ አንብቡ። በጥቅሱ ላይ የሚገኘውን መሠረታዊ ሥርዓት የሚያጎላ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ለማሰብ ሞክሩ። ከዚያም መሠረታዊ ሥርዓቱን በሕይወታችሁ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት አድርጉ። በአምላክ ቃል ላይ ተመሥርታችሁ ውሳኔዎችን ማድረጋችሁ፣ ሕይወታችሁን በዚያ መሠረት ለመምራትና ከቃሉ እውነተኛ ጥቅም ለማግኘት ይረዳችኋል።—መዝ 119:105
በዓለም ዙሪያ ያሉ የቤቴል ቤተሰብ አባላት በየቀኑ ቁርስ ሰዓት ላይ ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር በተባለው ቡክሌት ላይ ይወያያሉ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከእነዚህ የማለዳ አምልኮ ፕሮግራሞች ውስጥ አንዳንዶቹ JW ብሮድካስቲንግ ላይ ፕሮግራሞች እና ዝግጅቶች በሚለው ሥር መውጣት ጀምረዋል። እነዚህን ፕሮግራሞች ለመጨረሻ ጊዜ የተመለከታችሁት መቼ ነው? ምናልባትም በእነዚህ ፕሮግራሞች ላይ ከወጡት ትምህርቶች ውስጥ አንዳንዶቹ በቀጥታ እናንተን የሚመለከቱ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ስለ ሎጥ የሚናገረውን ዘገባ መመርመራችሁ በውሳኔያችሁ ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?
ዓለምን አትውደዱ (1ዮሐ 2:15) የተባለውን ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦
ቀኑን ሙሉ ለይሖዋ ቃል ትልቅ ቦታ እንደምሰጥ ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?