ክርስቲያናዊ ሕይወት
ሌሎች ሲያሞግሷችሁ ትሑት ሁኑ
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሊያሞግሱን ወይም ሊያመሰግኑን ይችላሉ። ሰዎች በተገቢ ምክንያት ተነሳስተው ከልባቸው ካመሰገኑን ልንበረታታ እንችላለን። (ምሳሌ 15:23፤ 31:10, 28) ሆኖም የሰዎች ሙገሳ ራሳችንን ከፍ ከፍ እንድናደርግና የኩራት ስሜት እንዲያድርብን እንዳያደርገን መጠንቀቅ ይኖርብናል።
እንደ ኢየሱስ ታማኝ ሁኑ—ሌሎች ሲያሞግሷችሁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ሰዎች ስለ ምን ጉዳይ ሊያሞግሱን ይችላሉ?
ወንድሞች ሰርጌን ያሞገሱት እንዴት ነው?
ሙገሳቸው ከተገቢው ያለፈው እንዴት ነው?
ሰርጌ በትሕትና መልስ ከሰጠበት መንገድ ምን ትምህርት አግኝተሃል?