ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—በስልክ መመሥከር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የስልክ ምሥክርነት ‘ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ ለመመሥከር’ የሚያስችል ግሩም ዘዴ ነው። (ሥራ 20:24)a ሰዎችን በአካል ሄደን ማነጋገር በማንችልበት ጊዜ ምሥክርነት ለመስጠት ያስችለናል።
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
ተዘጋጁ። ተገቢ የሆነ ርዕሰ ጉዳይ ምረጡ። ከዚያም የምትናገሩትን ሐሳብ የያዘ ማስታወሻ አዘጋጁ። በተጨማሪም ስልኩ ካልተነሳ የድምፅ መልእክት መተው እንድትችሉ የደወላችሁበትን ምክንያት የሚገልጽ አጭር መልእክት ማዘጋጀት ትችላላችሁ። ስልክ ስትደውሉ ማስታወሻችሁንና ሌሎች የሚያስፈልጓችሁን መሣሪያዎች ጠረጴዛ ላይ ማስቀመጣችሁ ጠቃሚ ነው፤ ለምሳሌ በኤሌክትሮኒክ መሣሪያችሁ ላይ JW Library® ወይም jw.org® ከፍታችሁ ማዘጋጀት ትችላላችሁ
ዘና በሉ። ተፈጥሯዊ አነጋገራችሁን ተጠቀሙ። ግለሰቡ ቢያያችሁ ኖሮ እንደምታደርጉት ፈገግ በሉ እንዲሁም አካላዊ መግለጫዎችን ተጠቀሙ። ሳያስፈልግ ረዘም ላለ ጊዜ ዝም አትበሉ። እንዲሁም ከሌሎች ጋር ማገልገል ጠቃሚ ነው። የምታነጋግሩት ሰው ጥያቄ ከጠየቃችሁ ጥያቄውን ጮክ ብላችሁ ድገሙት፤ ይህም የአገልግሎት ጓደኛችሁ መልስ በመፈለግ እንዲረዳችሁ ያስችላል
ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣሉ። ግለሰቡ ፍላጎት ካሳየ በቀጣዩ ጊዜ ስትደውሉለት የምትወያዩበትን ጥያቄ ጠይቁት። በተጨማሪም አንድ ጽሑፍ በኢ-ሜይል ወይም በፖስታ ልትልኩለት አሊያም በአካል ልትወስዱለት እንደምትችሉ ልትነግሩት ትችላላችሁ። አንድ ቪዲዮ ወይም ጽሑፍ በኢ-ሜይል አሊያም በጽሑፍ መልእክት አማካኝነት እንደምትልኩለት ልትነግሩትም ትችላላችሁ። አመቺ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ በድረ ገጻችን ላይ የሚገኝን አንድ ገጽ ልትጠቁሙት ትችሉ ይሆናል
a በአካባቢያችሁ የስልክ ምሥክርነት መስጠት የሚቻል ከሆነ ከግል መረጃ ደህንነት ጋር የተያያዙ ሕጎችን በማይጥስ መልኩ መደረግ ይኖርበታል።