የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 53
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መናፍስት በምድር ላይ ኖረው በኋላ የሞቱ ሰዎች አይደሉም
    የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
    ንቁ!—2007
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ጥያቄ 2፦ ስሞት ምን እሆናለሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 53

ስንሞት ምን እንሆናለን?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ “ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም” ይላል። (መክብብ 9:5፤ መዝሙር 146:4) በመሆኑም ስንሞት ሕልውናችን ያከትማል ማለት ነው። የሞቱ ሰዎች ማሰብም ሆነ መሥራት አይችሉም፤ እንዲሁም ምንም ዓይነት ስሜት የላቸውም።

“ወደ ዐፈር ትመለሳለህ”

አምላክ፣ ስንሞት ምን እንደምንሆን ለመጀመሪያው ሰው ማለትም ለአዳም ነግሮታል። አዳም ታዛዥ ባለመሆኑ አምላክ “ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ” ብሎታል። (ዘፍጥረት 3:19) አምላክ አዳምን “ከምድር ዐፈር” ከመፍጠሩ በፊት አዳም ሕልውና አልነበረውም። (ዘፍጥረት 2:7) ስለሆነም አዳም ሲሞት ወደ አፈር ተመለሰ፤ በሌላ አባባል ሕልውናው አከተመ።

በዛሬው ጊዜም አንድ ሰው ሲሞት የሚያጋጥመው ነገር ተመሳሳይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎችንም ሆነ እንስሳትን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉም ከዐፈር እንደ ሆኑ፣ ተመልሰው ወደ ዐፈር ይሄዳሉ።”​—መክብብ 3:19, 20

ሞት የሁሉ ነገር መጨረሻ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን ብዙውን ጊዜ ከእንቅልፍ ጋር ያመሳስለዋል። (መዝሙር 13:3፤ ዮሐንስ 11:11-14፤ የሐዋርያት ሥራ 7:60) ከባድ እንቅልፍ ውስጥ ያለ ሰው በአካባቢው ስለሚከናወነው ነገር ምንም አያውቅም። በተመሳሳይም የሞቱ ሰዎች ምንም ነገር አያውቁም። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የሞቱ ሰዎችን ከእንቅልፋቸው የማንቃት ያህል እንደሚቀሰቅሳቸውና መልሶ ሕይወት እንደሚሰጣቸው ይናገራል። (ኢዮብ 14:13-15) አምላክ ከሞት ለሚያስነሳቸው ሰዎች ሞት የሁሉ ነገር መጨረሻ አይደለም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ