መዝሙር 14
ሁሉንም ነገር አዲስ ያደርጋል
በወረቀት የሚታተመው
1. የአምላክ መንግሥት መግዛቱን ጀምሯል።
የይሖዋ ልጅ ሥልጣኑን ይዟል።
የሰማይ ጠላቶቹን ድል አ’ርጓል፤
የምድሮቹንም ቶሎ ያጠፋል።
(አዝማች)
ተስፋው እንዴት ያስደስታል!
አምላክ ከሰዎች ጋር ያድራል።
ሐዘን፣ ለቅሶ ፍጹም አይኖርም፤
ሞት ይጠፋል እስከ ዘላለም፤
‘ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ’ ብሏል፤
እውነት ነው ይፈጸማል።
2. አዲሷን ’የሩሳሌም ይዩ ሰዎች፤
የበጉ ሙሽራ ተውባለች።
የከበረ ዕንቁ ሰጣት ድምቀት፤
ይሖዋ አምላክ ሆነላት መብራት።
(አዝማች)
ተስፋው እንዴት ያስደስታል!
አምላክ ከሰዎች ጋር ያድራል።
ሐዘን፣ ለቅሶ ፍጹም አይኖርም፤
ሞት ይጠፋል እስከ ዘላለም፤
‘ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ’ ብሏል፤
እውነት ነው ይፈጸማል።
3. በሮቿ የማይዘጉ ቀን ከሌት፤
ይቺ ከተማ የሰው ልጅ ሐሴት።
ከሷ በሚፈነጥቀው ብርሃን፣
ሕዝቦች ይጓዙ ዓይተው ጸዳሏን።
(አዝማች)
ተስፋው እንዴት ያስደስታል!
አምላክ ከሰዎች ጋር ያድራል።
ሐዘን፣ ለቅሶ ፍጹም አይኖርም፤
ሞት ይጠፋል እስከ ዘላለም፤
‘ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ’ ብሏል፤
እውነት ነው ይፈጸማል።
(በተጨማሪም ማቴ. 16:3ን፣ ራእይ 12:7-9፤ 21:23-25ን ተመልከት።)