መዝሙር 118
አንዳችን ሌላውን መቀበል
በወረቀት የሚታተመው
(ሮም 15:7)
1. የአምላክን ቃል ለመስማት ብለው፣
የመጡትን ’ንቀበላቸው።
ጋብዞናል ሕይወት ሰጪውን እውነት፤
ለጥሪው ምላሽ ’ንስጥ በአመስጋኝነት።
2. ይመስገን አምላክ ወንድሞች ሰጠን፤
ሁሌም በደስታ ’ሚቀበሉን።
እናክብራቸው እንዲህ ያሉትን፤
እኛም እንቀበል እንግዶቻችንን።
3. ቅኖች እውነትን መጥተው ’ንዲማሩ፣
ለሰው ሁሉ ተከፍቷል በሩ።
አምላክ ስቦናል በልጁ በኩል፤
ስለዚህ ሌሎችን ከልብ እንቀበል።