የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 9 ገጽ 12
  • በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ማስተማር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ማስተማር
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሚታዩ ነገሮች አስደግፎ ማስተማር
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • የቪዲዮ ፊልሞቻችንን ተጠቅማችሁ አስተምሩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን በቪዲዮ ተጠቅማችሁ አስተምሩ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ኤድስ የያዛቸውን ሰዎች መርዳት
    ንቁ!—1995
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 9 ገጽ 12

ጥናት 9

በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ማስተማር

ጥቅስ

ዘፍጥረት 15:5

ፍሬ ሐሳብ፦ በሚታዩ ነገሮች በመጠቀም፣ አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን ግልጽና ቀላል በሆነ መንገድ አስተምር።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ትምህርቱን ይበልጥ ግልጽ የሚያደርጉ ነገሮችን ተጠቀም። ዋና ዋና ነጥቦችን ለማጉላት ሥዕሎችን፣ ካርታዎችን፣ የጊዜ ሰሌዳዎችን ወይም ሌሎች የሚታዩ ነገሮችን ተጠቀም። እርግጥ በጣም አስፈላጊ ላልሆኑ ነጥቦች ይህን ማድረግ አያስፈልግም። አድማጮችህ፣ ለማስተማሪያነት የተጠቀምክበትን ነገር ብቻ ሳይሆን ማጉላት የፈለግከውን ነጥብም እንዲያስታውሱ እርዳቸው።

  • ለማስተማር የምትጠቀምበት ነገር ለአድማጮችህ በደንብ የሚታይ ሊሆን ይገባል።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    ለማስተማሪያነት ልትጠቀምባቸው ያሰብካቸውን ነገሮች አስቀድመህ አዘጋጅ።

ለአገልግሎት

ለምታነጋግረው ሰው በጽሑፎቻችን ላይ የሚገኘውን ሥዕል ካሳየኸው በኋላ ሐሳቡን እንዲገልጽ ጠይቀው። ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን ለማጉላት እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ጥያቄዎችን መጠየቅ ትችላለህ። ቪዲዮ የምታሳየው ከሆነ ስክሪኑን ወደ እሱ አዙረው። አብዛኛውን ጊዜ፣ ቪዲዮው እየተጫወተ እያለ መናገር አስፈላጊ አይደለም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ