ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 12
ፋሲካ ለክርስቲያኖች ምን ትርጉም አለው?
እስራኤላውያን አሥረኛው መቅሰፍት እንዳይደርስባቸው ከፈለጉ የይሖዋን መመሪያ የግድ መታዘዝ ነበረባቸው። (ዘፀ 12:28) ኒሳን 14 ምሽት ላይ እስራኤላውያን ቤተሰቦች በየቤታቸው እንዲሰበሰቡ ታዘው ነበር። አንድ ዓመት የሞላው ጤናማ የበግ ወይም የፍየል ጠቦት ማረድ ነበረባቸው። ከዚያም ደሙን በበራቸው ጉበንና መቃኖች ላይ ይረጩታል። ቀጥሎም የበጉን ወይም የፍየሉን ሙሉ አካል በመጥበስ በጥድፊያ መብላት ነበረባቸው። እስኪነጋ ድረስ ማንም ሰው ከቤቱ መውጣት አልነበረበትም።—ዘፀ 12:9-11, 22
በዛሬው ጊዜ ታዛዥነት በየትኞቹ መንገዶች ጥበቃ ያስገኝልናል?