መዝሙር
የዳዊት ማህሌት፤* ከልጁ ከአቢሴሎም በሸሸ ጊዜ።+
3 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ እንዲህ የበዙት ለምንድን ነው?+
ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ የተነሱትስ ለምንድን ነው?+
2 ብዙዎች “አምላክ አያድነውም” እያሉ
4 ድምፄን ከፍ አድርጌ ይሖዋን እጣራለሁ፤
እሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል።+ (ሴላ)
6 በየአቅጣጫው የተሰለፉብኝን
በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልፈራም።+
7 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! አምላኬ ሆይ፣ አድነኝ!+
የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህና፤
የክፉዎችን ጥርስ ትሰባብራለህ።+
8 ማዳን የይሖዋ ነው።+
በረከትህ በሕዝብህ ላይ ነው። (ሴላ)