መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት ማህሌት።
4 ጻድቅ አምላኬ ሆይ፣+ ስጣራ መልስልኝ።
በምጨነቅበት ጊዜ ማምለጫ መንገድ* አዘጋጅልኝ።
ቸርነት አሳየኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።
2 እናንተ የሰው ልጆች፣ ክብሬን ወደ ውርደት የምትለውጡት እስከ መቼ ነው?
ከንቱ ነገሮችን የምትወዱት እስከ መቼ ነው? ሐሰትንስ የምትሹት እስከ መቼ ነው? (ሴላ)
3 ይሖዋ ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ልዩ በሆነ መንገድ እንደሚይዘው እወቁ፤*
ይሖዋ በጠራሁት ጊዜ ይሰማኛል።
4 ተቆጡ፤ ሆኖም ኃጢአት አትሥሩ።+
የምትናገሩትን በመኝታችሁ ላይ ሳላችሁ በልባችሁ ተናገሩ፤ ጸጥም በሉ። (ሴላ)
5 የጽድቅ መሥዋዕቶች አቅርቡ፤
በይሖዋም ታመኑ።+
6 “መልካም ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች አሉ።
ይሖዋ ሆይ፣ የፊትህን ብርሃን በላያችን አብራ።+
7 የተትረፈረፈ እህል ከሰበሰቡና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ካመረቱ ሰዎች ይበልጥ
ልቤ በሐሴት እንዲሞላ አደረግክ።